ደማችን ለመከላከያችን

 “ ደማችን ለመከላከያ  ሠራዊታችን“

በሙሉጎጃም አንዱዓለም

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በፕሬዘዳንቱ መሪነት “ደማችን ለመከላከያችን“ በተሰኘው የደም ልገሳ መርሀ ግብር እየተሳተፉ ነው፡፡

ለመከላከያ ሰራዊታችን አገልግሎት የሚውል ደም ለመሰብሰብ አገራዊ ጥሪ መደረጉን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ5ኛ ዓመት ተማሪና የኢትዮጲያ ህክምና ተማሪዎች ማህበር-ባህርዳር አባል ተማሪ መላኩ አዳነ እንደገለፀው የባሕር ዳር ደም ባንክ አገልግሎት መርሀ-ግብሩን በባለቤትነት ቢይዘውም ሁሉም ከመከላከያ ሰራዊታችን ጎን መሆኑን ለማሳየት በራሱ ተነሳሸነት ደም እየለገሰ ነው ብሏል፡፡