የግንባታ መረጃ ሞዴሊንግ ስልጠና ተጠናቀቀ

ለ20 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የግንባታ መረጃ ሞዴሊንግ ስልጠና ተጠናቀቀ

**********************************************************

[ህዳር 13/2015 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ] በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት Building Information Model (BIM) ቴክኖሎጂን በኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው ማካተትን አልሞ ለመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት አርክቴክቸር ትምህርት ክፍል መምህራን፣ ለአማራ ዲዛይን ቢሮ ባለሙያዎች፣ ለፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራን ለ20 ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

በመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት አርክቴክቸር ትምህርት ክፍል ኃላፊ አቶ ታደለ ይኸይስ ስልጠናውን አስመልክተው እንደገለጹት ስልጠናው የተጀመረው ባለፈው አመት በመሬት አስተዳደር ኢንስቲትዩት እና በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት መካከል በጋራ ለመስራት በተስማሙት መሰረት መሆኑን ገልፀውልናል፡፡

አቶ ታደለ የስልጠናው ዋና አላማ የBIM ቴክኖሎጂን እያንዳንዱ ባለሙያ በመማር ማስተማሩ ሂደት እንዲያካትተው፣ የዩኒቨርስቲው መምህራን ቀሪ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን የሚያሰለጥኑበት ማዕከላት እንዲቋቋሙ ማመቻቸት እና ከመማር ማስተማር ባሻገር የግል ቢሮ ያላቸው መምህራን በስራቸው አጋጣሚ ሁሉ የBIM ቴክኖሎጂን ተግባራዊ እንዲያደርጉ እንዲያግዝ ነው ብለዋል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ባለሙያ አቶ ፈለቀ አሰፋ ስለስልጠናው ሲናገሩ የግንባታ መረጃ ሞዴሊንግ ወይም Building Information Model (BIM) ቴክኖሎጂን የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ከእቅድ እስከ ማፍረስ ያለውን የግንባታ ስርዓት አቀናጅቶ መስራት የሚችል ሲሆን ይህ ቴክኖሎጂ እንደ አገር በ2017 ዓ.ም አስገዳጅ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ ስለዚህ ዩኒቨርሲቲዎች በካሪኩለም ያካትታሉ፣ የስልጠና ማዕከላት በማቋቋም የስልጠና ፍላጎት እንዲያሟሉ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

አቶ ፈለቀ ስልጠናው ዲዛይን እና ግንባታው ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ፕሮጀክቶቻቸውን በBIM ቴክኖሎጂ እንዲያስገቡ እድል ይፈጥራል፡፡ ይህ ማለት ቴክኖሎጂውን ስንተገብር ኢንዱስቲሪው ላይ የሚፈጠረውን የጥራት፣ ያልተፈለገ ወጪ፣ የጊዜ ብክነት እና አለመናበብ  ችግሮችን ሁሉ መቅረፍ እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

 

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

-------------------------------------

``ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ``

``Wisdom at the source of Blue Nile``

Thank you for visiting, inviting and sharing our Pages!

Thank you for your likes and comments too!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram www.instagram.com/bduethiopia

TikTok https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram https://t.me/bduethiopia

Twitter https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/