የክህሎት ስልጠና

ለተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

በሙሉጎጃም አንዱዓለም

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቢሮ ከማህበራዊና ጤና አገልግሎት ልማት ድርጅት ጋር በመተባበር ለመደበኛ ተማሪዎች  በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ለ2 ተከታታይ ቀናት የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

የስልጠናውን የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የሴቶች፣ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ ብርሃኔ መንግስቴ የስልጠናው ዋና ዓላማ ተማሪዎች እራሳቸውን እንዲያውቁ፣በራስ መተማመናቸውን እንዲያዳብሩ  እንዲሁም ከስልጠናው ያገኙትን ክህሎት ለሌሎች በማጋራት ባሉበት ግቢ አምባሳደር ሆነው እንዲያገለግሉ ታልሞ መሆኑን ገልፀዋል፡፡  

ዳይሬክተሯ አክለውም ከአሁን በፊት የነበረው አሰራር የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እንደገቡ ስልጠናው ይሰጥ እንደነበር ጠቁመው በያዝነው ዓመት ግን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አንደኛ ዓመት ተማሪዎች በመዘግየታቸው በመማር ላይ ላሉት በተለይም በክበባት የታቀፉ ሆነው  ከሁሉም ግቢና ባች ለተውጣጡ ተማሪዎች ስልጠናው መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

ማህበራዊና ጤና አገልግሎት ልማት ድርጅት ከዩኒቨርሲቲው ጋር አብሮ ለመስራት በያዘው ውል መሰረት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነና የተለያዩ ስልጠናዎችንም ለተለያዩ አካላት በመስጠት ላይ እንደሆነ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ 

አሰልጣኞችም ከአሁን በፊት የህይዎት ክህሎት ስልጠና የወሰዱ የዩኒቨርሲቲው መምህራን መሆናቸው ተገልጿል፡፡