የተማሪዎች ፈጠራ ስራዎች

የተማሪዎች ፈጠራ ስራ ለዕይ ታቀረበ
*******************************
(ሀምሌ 24/2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-BDU) የባሕር ዳር ሳይንስ ኢንኩቤሽን ማዕከል/STEM/ ተማሪዎች በscience project, Calculator for blind people, ICT projects, Electronics and Rebottles, Preventing drunk driving, payroll formulation ላይ የሠሯቸው የፈጠራ ስራዎች የተማሪ ወላጆች እና ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት ለዕይታ ቀረቡ፡፡
 
በስነ-ስርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳት ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራው ወላጆች የልጆቻቸውን የፈጠራ ውጤት እንዲያዩ እና ለቀጣይ እንዲያበረታቷቸው ሌሎች ደግሞ ይህን በማየት እንዲነሳሱ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ተስፋዬ አክለውም በዚህ ማዕከል የሚማሩ ተማሪዎች ከመደበኛ ትምህርት ቤቶች ከሚማሩ ተማሪዎች በተሻለ መልኩ እንዲሰሩ፣ ፈጠራ እንዲፈጥሩ ታስቦ ሲሆን ተማሪዎች በማዕከሉ ፕሮጀክት የማይሰሩ ከሆነ መቀጠል እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡
የባሕር ዳር ሳይንስ ኢንኩቤሽን ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ተስፋ ተገኘ በበኩላቸው በማዕከሉ ስድስት ፕሮግራሞች መኖራቸውን ሲጠቅሱ ከ9ኛ ክፍል ጀምሮ ባሕር ዳር ከሚገኙ የተለያዩ ት/ቤቶች በየዓመቱ 50 ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል እንዲሁም ከ5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሳይንስን በተግባር ለ45 ቀናት ስልጠና ይሰጣል፡፡
ባሕር ዳር እና በአካባቢው የሚገኙ 2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች አምስት አምስት ሴት ተማሪዎች ተመርጠው በዩኒቨርሲቲው ለ9 ቀናት በሰሚስተር በሚኖረው እረፍት ሳይንስን በተግባር እየተማሩ ከሌሎች ጋር አብሮ የመኖርን ልምድ ይቀስማሉ፣ ማዕከሉ በአገር አቀፍ ደረጃ በሚደረገው የፈጠራ ስራ ውድድር እንዲሳተፉ ድጋፍ ያደረጋል፣ የህፃናት ፕሮግራም ከ4ኛ እስከ 6ኛ ለሚማሩ ተማሪዎች በቅዳሜ እና እሁድ ቀናቶች ያሰለጥናል፣ባሕር ዳር እና አካባቢው የሚገኙ ተማሪዎች ቤተ ሙከራውን መጠቀም ሲፈልጉ ቀድመው ያሳውቁና ማዕከሉ ውስጥ እንዲሰሩይደረጋል ብለዋል ዶ/ር ተስፋ፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ-BDU
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ
Wisdom at the source of Blue Nile
Thank you for visiting our page!
ለተጨማሪመረጃዎች፡-
Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official
website :- www.bdu.edu.et
#BDU60th_ANNIVERSARY