የተማሪዎች ምዝገባ

የተማሪዎች ምዝገባ
ባዳዩ፣ 03/05/2014 ዓ.ም
-----------------------
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በህልውና ዘመቻው ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል ምዝገባ እያካሄዱ ነው፡፡
 
ተማሪዎች እንደገለፁት ትምህርታቸውን ለመጀመር የዩኒቨርሲቲውን ጥሪ በጉጉት ይጠብቁት እንደነበርና ዩኒቨርሲቲው ጥሪ ሲያስተላልፍ ጥሪውን በደስታ ተቀብለው መምጣታቸውን ተናግረዋል፡፡
 
ተማሪዎች ሲገቡ አስፈላጊውን አልባሳት በመያዝ ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀላቸው የመኝታ ክፍል እየገቡ ሲሆን ምዝገባው ያለምንም ተግዳሮት በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ የምግብ አገልግሎቱም ከትናንትና ምሳ ሰዓት ጀምሮ እየተሰጠ በመሆኑ ተማሪዎች ወደ መደበኛ የዩኒቨርሲቲ ሕይዎታቸው በመመለስ ላይ ይገኛሉ፡፡ የዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራሮችም በየግቢው ተዟዙረው የተማሪዎችን መግባት ተመልክተዋል፡፡
በሙሉጎጃም አንዱዓለም