የባሕር ዳር ከተማ መሰረተ ልማት

የባሕር ዳር ከተማን መሰረተ ልማት ዲጂታል ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በትዕግስት ዳዊት

የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የባሕር ዳር ከተማን ዲጂታል መሰረተ ልማት ለማዘጋጀት የሁለት ቀን አውደ ጥናት በባሕር ዳር አካሂደዋል።

በአውደ ጥናቱ ላይ የተገኙት Dr. Lara, Allen ከ ‘University of Cambridge and the Center for Global Quality’ የመጡ ሲሆን  Dr. Lara ካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት የተፈራረማቸውን ፕሮግራሞች አስተዋውቀው ከእነዚህ ፕሮግራሞች አንዱ የሆነው የባሕር ዳር ከተማን መሰረተ ልማት ዲጂታል ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።

በመርሃ ግብሩ የተገኙት ዶ/ር ሰብስበው አጥቃው, Commissioner, The Science, Technology Information and Communications Commission, Amhara National Regional State) ሲሆኑ ‘Over view of ICT in the Amhara Region’ የሚል ርዕስ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን በዚህና በሌሎች ወረቀቶች ላይ ሀሳቦች ተነስተው ሰፋ ያለ ውይይት በተሳታፊዎች ተደርጓል።

በአውደ ጥናቱ ከእንግሊዝ፣ ከኔዘርላንድስ፣ ከኬንያ እንዲሁም ከአዲስ አበባና ከባሕር ዳር የመጡ ምሁራን እውቀታቻውንና ልምዳቸውን ያካፈሉ ሲሆን ከኢትዮጵያ ውጭ የመጡት ምሁራን የየሀገራቸውን ልምዶች አቅርበዋል። የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ባሕር ዳር ከተማ አዲስና ዲጂታል መሰረተ ልማት እንደሚያስፈልጋት በማመኑና ለመስራት በመነሳሳቱ ዲጂታል መሰረተ ልማት ለማዘጋጀት መታሰቡ ተገልጿል።