የባሕር ዳር ከተማን የዲጂታል አድራሻ ስርዓት ለመዘርጋት

የባሕር ዳር ከተማን የዲጂታል አድራሻ ስርዓት ለመዘርጋት እንቅስቃሴ ተጀምሯል።

የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፖሻል ኢንስቲትዩት የባሕር ዳር  ከተማን የዲጂታል አድራሻ ስርዓት ለመዘርጋት ከከተማ አስተዳደሩ እና ከባሕር ዳር  ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱ የዲጂታል አድራሻ ስርዓት ፕሮጀክቱ ተግባራዊ መደረግ የከተማዋን የቱሪዝም ሃብት በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ እና ከቱሪዝም የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ እንዲሁም የዲጂታል ኢኮኖሚውን በማነቃቃትና በመገንባት ከተማዋን ለኢንቨስትመንት ምቹና ተመራጭ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገልጿል።

የከተማዋን የዲጂታል አድራሻ ስርአት ለመገንባት በከተማዋ የሚገኙ መኖርያ ቤቶች እና ተቋማትን ፣የመንገድና ትራንስፖርት ፍሰት መረጃን ለመተንተን ፣የዲጂታል አድራሻ ካርታን እና ሲስተምን ለመዘርጋት፣ የንግድ ተቋማት መገኛና አቅጣጫ ጠቋሚን በዲጂታል ለማገዝ፣የመሬት አስተዳደር እና ሌሎች የከተማዋን መረጃዎች ለማዘመን እንደሚረዳ ተነስቷል።

የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ በላቸው ጽሐይ የባሕር ዳር  ከተማ አስተዳደር እና ዩኒቨርሲቲ የከተማዋን የዲጂታል አድራሻ ስርአት ለመገንባት ያሳዩትን ፍላጎት እና በዘርፉ ያሉ ጅምሮችን አድንቀው የዲጂታል አድራሻ ስርአት የሀገርን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውጤታማ ለማድረግ ያለውን ሚና አብራርተዋል።

የባሕር ዳር  ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አስሜ ብርሌ የፕሮጀክቱ መተግበር የከተማውን ማህበረሰብ ኢኮኖሚያዋ እና ማህበራዊ እንቅስቃሴ ለማቅለል ብሎም የቱሪዝም ገበያውን ለማገዝ ከፍተኛ ሚና ያለው በመሆኑ በቅርብ ጊዜ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራ አንስተዋል።

የባሕር ዳር  ዩኒቨርሲቲ ጂኦስፓሻል ዳታ እና ቴክኖሎጂ ሴንተር (GDTC) ዳይሬክተር ዶ/ር ዳንኤል አያሌው በዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም የተሰሩ የከተማዋን የቱሪስት ፍሰት የሚያሳዩ መተግበሪያዎች እና ሌሎች የዲጂታል ጅማሮዎችን እና አቅሞች እንደ መነሻ በመውሰድ በፕሮጀክቱ ውጤታማ ስራ ለመስራት ዩኒቨርሲቲው በሙሉ አቅሙ እንደሚያግዝ አንስተዋል።

የስፔስ ሳይንስና ጂኦስፖሻል ኢንስቲትዩት የከተሞችን የዲጂታል አድራሻ ስርዓት ለመዘርጋት በያዝነው የበጀት አመት ለ6 ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ ሲሆን የቢሾፍቱ እና አዳማ ከተሞች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል።

@space science and Geo - Spatial Institute