የሴት ተማሪዎች ስልጠና

ለሴት ተማሪዎች ስልጠና ተሠጠ

ከባህር ዳር ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተሰባሰቡ 25 የ10ኛ ክፍል ተማሪዎች Girls Can Code next generation በሚል መሪ ሃሳብ ለ20 ቀን የቆየ የሂሳብ ስልጠና በክረምቱ መርሃ ግብር በፔዳ ግቢ ተሰቷል ፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ከአሜሪካ ኤምባሲ እና I Cog Labs ጋር በመተባበር የተዘጋጀው ይህ ስልጠና ዩኒቨርሲቲው ከሚሰራቸው የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት ውስጥ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የሴት ተማሪዎችን አቅም የማጎልበት እቅዱ አንዱ ማሳያ እንደሆነም ታውቋል፡፡በተያያዘም ሀገሪቷ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለምታደርገው ሽግግር ማዕከሉ በቴክኖሎጂ ፈጠራ የተካነ የሰው ሀይል ለማፍራት አልሞ እየሰራ እንደሆነና ይህን መሰል ስልጠናዎችም እቅዱን በማሳካት ረገድ ድርሻ እንደሚኖራቸው ተጠቁሟል፡፡