ሰላምንና ደህንነትን ማጎልበት

በትምህርትና በውይይት ሰላምንና ደህንነትን በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ማጎልበት​ በሚል ርእስ ስልጠና ተሰጠ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ከአሜሪካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከአምሳ በላይ የሚሆኑ የሰላም ፎረም ተማሪዎችና የተማሪ ህብረት ተወካዮች በተገኙበት I declare Peace በሚል መሪ ቃል ስልጠና ተካሂዷል፡፡

በስልጠናው ተማሪዎች የሚከተሉት ሁለት ጥያቄዎች ላይ በቡድን ውይይት እድርገዋል፡ 1. ሰላምን በማስፈንና ቀጣዩነቱን በማጋገጥ ረገድ የትምህርት ተቋማት(ተማሪዎችና መምህራን) ምን ቁልፍ ሚና መጫወት ይችላሉ;

2. ሰላምን በሀገር አቀፍም ሆነ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደረጃ ለማረጋገጥ ምን አይነት ስልት መጠቀም ይቻላል

በስልጠናው ከትምህርት እና ስነ ባህሪ ኮሌጅ ዶ/ር አንዳርገቸው ሞገስ እና አቶ መሰረት አያሌው፣ ከቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አቶ ዘውዱ ላቀ ባቀረቡት መነሻ ፅሁፍ ላይ በመመርኮዝ ውይይጥ ተደርጓል፡፡

በመጨረሻም ተሳታፊዎች በቀጣይ ችግሮች እንዳይከሰቱ ለማድረግ በእለቱ የተሰጠውን ስልጠና የመሰሉ ተከታታይ ስልጠናዎችን በሌሎች ክልል እና ዩኒቨርስቲዎች ለሚገኙ ተማሪዎች እንዲሰጥ አሳስበዋል፡፡