ሰላማዊ የዩኒቨርሲቲ ድባብ

ሰላማዊ የዩኒቨርሲቲ ድባብ ለመፍጠር የሚያግዝ ሰነድ ቀረበ

ሰላማዊ የዩኒቨርሲቲ ድባብ ለመፍጠር የሚያግዝ ሰነድ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሳይኮሎጂ ት/ክፍል ባልደረባ በሆኑት አቶ ታምሩ ደለለኝ የቀረበ ሲሆን የሰነዱ አላማ በዩኒቨርሲቲዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን በመቀነስ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ለመረጋገጥ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ ለዚህም የተማሪዎችን ዐዕምሮዊ፣ስነ-ልቦናዊ ና ሰነ-ምግባራዊ ሰብዕናን መገንባት አስፈላጊ እንደሆነ ተጠቁሟል።
ስለሆነም ተማሪዎች ከክፍል ዉሰጥ ከሚሰጣቸዉ መደበኛ ትምህርት በተጨማሪ በግቢ ውስጥና ከግቢ ዉጭ በበጎ ፍቃድ አገልግሎት፣ በትምህርታዊ ክለባት: በፈጠራ ና ሰፓርታዊ ዉድድር፣ በሙዚቃ፣ ድራማና ተዛማጅ የጥበብ ስራዎች፤ እንዲሁም ትምህርታዊ ዉይይት ና ክርክር ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ በማገዝ ተማሪዎች ይዘዉት ከመጡት ነጠላዊ ማንነት(mono/singular identity) ባሻገር ሌሎች ማንነቶችን እንዲያዳብሩ ማድረግ እንደሚገባ ተብራርቷል።የታሰበዉን አላማ ለማሳካትም ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እንደሚያስፈልግ ተገለፆል።
በቀረበዉ ሰነድ ላይ በርካታ ገንቢ አሰተያየቶች የቀረቡ ሲሆን በእለቱ ታዳሚ የነበሩት የዩኒቨርሲቲ ዉ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬዉ ተገኘ ተመሳሳይ መድረክ ለመምህራን እና የአሰተዳደር ሰራተኞች መዘጋጀት እንዳለበት ጠቁመዉ የቀረቡ አሰተያየቶች ሰነዱን ለማዳበር እንደሚያግዙ በመግለፅ ተሳታፊዎችን አድንቀዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለዉም ዩኒቨርሲቲ ዉን የሰላም ተቋም ማድረግ የሁሉም ሃላፊነት በመሆኑ ምንም ቅድመ ሁኔታዎች ሊያግደን አይገባም በማለት ጠንከር ያለ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም የትምህርታዊ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ ሰላማዊ መማር ማሰተማር ለማረጋገጥ ውጫዊ ተግዳሮቶች ተገማች ቢሆኑም ዩኒቨርሲቲ ዉ ባለዉ የሀላፊነት ወሰን ልክ ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዞ መስራት እንደሚገባ መልእክት አስተላልፈዋል። ከዚህ ባለፈ ውጫዊ ችግሮች የሚፈቱበትን አግባብ በተመለከተ በየደረጃዉ ላሉ አመራር አካላት በማቅረብ ሰላማዊ መማር ማስተማርን ማረጋገጥ እንደሚቻል እምነታቸውን አጋርተዋል፡፡
በእለቱ የመወያያ ሰነዱ ከመቅረቡ በፊት ‘Building a healthy institutional Ethos’ በሚል ርዕስ ዶ/ር ታደሰ አክሎግ ወረቀት ያቀረቡ ሲሆን በፅሁፋቸውም አቅራቢዉ የተማሪዎችን ሁለንተናዊ ስብዕና ለመገንባት ሁሉም የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት የጋራ እሴት(shared institutional ethos) ሊኖራቸዉ እንደሚገባ በመጠቆም፤ በዚህ ዙሪያ የተሻለ ተሞክሮ ያለዉን የጅዋራላል ዩኒቨርሲቲ (’ Jawaralal Nehru University’/JNU) ዩኒቨርሲቲ ልምድ አብራርተዋል።

በውይይት መድረኩ ከበላይ አመራሩ ተጨማሪ ዲኖች ና ትምህርት ክፍል ሃላፊዎች ታድመዋል።