ለኮካ ኮላ ስልጠና

ለኮካ ኮላ ኩባንያ ሠራተኞች ስልጠና ተሰጠ
=======================

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አደጋ መከላከልና ዘላቂ ልማት ትምህርት ክፍል መምህራን በባህር ዳር ከተማ ለሚገኘው በኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ካምፓኒ በተለያየ ዲፖርትመንት ውስጥ ለሚሠሩ 21 የድርጅቱ ሠራተኞች ድንገተኛ ዕሳት አደጋን እንዴት መከላከል ይቻላል በሚል ርዕስ ለአንድ ሳምንት ያህል በተግባር የተደገፈ ስልጠና ሠጥቷል፡፡

ዶ/ር ዘሪሁን ዮሐንስ በአደጋ መከላከልና ዘላቂ ልማት ትምህርት ክፍል የትምህርት ጥራትና ማረጋገጫ አስተባባሪ እንዳሉት ተቋሙ የአጭር ጊዜ ስልጠናዎችን ለድርጅቶችና ለተለያዩ ተቋማት ለመስጠት ስርዓተ-ትምህርት በመቅረጽ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ ዶ/ር ዘሪሁን አክለውም ከፌደራል የአደጋ መከላከል ኮሚሽን ጋር አብሮ ለመስራት ስምምነት ላይ በመደረሱ ወደፊት ከኮሚሽን መስሪያ ቤቱ ጋር በመሆን መሰል ተግባራትን በተጠናከረ መንገድ እንደሚያከናውኑ ጠቁመዋል፡፡

አቶ ይበልጣል ልየው በኮካኮላ ኩባንያ የሴፊቲ ኦፊሰር (safety officer ) ሲሆኑ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአደጋ መከላከል እና ዘላቂ ልማት ተቋም በጠየቃቸው መሠረት ስልጠናው መሠጠቱ እንዳስደሰታቸው ተናግረው ተቋሙ ከድርጅቱ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ስምምት በመፈራረም በአመት ሁለት ጊዜ ለድርጅቱ ሠራተኞች ስልጠና እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

ስልጠናውን የወሰዱ የድርጅቱ ሠራተኞች በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲ በንድፈ ሃሳብ የተማርነውን በተግባር በማየታችን ከድርጅታችን አልፈን በአቅራቢያችን የሚገኙ ተቋማትን፣ ድርጅቶችን በተለይም ክቡር የሆነውን የሠውን ልጅ ህይዎት እንድንታደግ ይረዳናል ብለዋል፡፡

ስልጠናውን የሠጡት 1. ዶ/ር ዘሪሁን ዮሐንስ 2. ሙሉነህ ጌታነህ 3. ወ/ሪት ፌሩዛ ተማም 4. የሚያምረው ዮሴፍ 5. ሔኖክ አባተ እና ዮሴፍ ታምሩ ሲሆኑ ሁሉም አሰልጣኞች በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አደጋ መከላከልና ዘላቂ ልማት ት/ት ክፍል መምህራን መሆናቸው ተገልጿል፡፡