የ MICE TOURISM ሳምንት ተከበረ

የዘንድሮውን የMICE Tourism ሣምንቱን ታሕሳስ 18/2009 በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን አቶ በላይነህ አሰሬ በይፋ የከፈቱት ሲሆኑ በዝግጅቱም መምህራን፣ የኮሌጅ ሰራተኞች እና ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡ የዝግጅቱ ባለቤት የሆኑት የሁለተኛ አመት የቱሪዝምና ሆቴል አስተዳደር ትምህርት ክፍል ተማሪዎችም የሀገራችንን የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች አልባሳትን በመልበስ ዝግጅቱን  እንዲደምቅ የበኩላቸውን አስተዋፆ አበርክተዋል፡፡ 

የ2009 ዓ.ም የMICE TOURISM በአሁኑ ሰዓት በፈጣን ዕድገት ላይ ከሚገኙ የሀገሪቱ የኢንዱስትሪ ዘርፎች ውስጥ አንዱ ሲሆን የተለያዩ ፋይዳዎችን በመጫወት ላይ ይገኛል፡፡  ለሀገር ኢኮኖሚ፣ ለተለያዩ መሰረተ ልማቶች መዘርጋት እንዲሁም ለህብረተሰቡ ላቅ ያለ ጥቅም እያስገኘ ያለ ዘርፈ ነው፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዙሀን ህዝቦች መኖርያ፣ የብዙ ቋንቋ ተናጋሪዎች ምድር አያሌ ተፈጥሮአዊ ባህላዊና ታሪካዊ የመስህብ ስፍራዎች ያሏት የሰው ዘር የነሉሲ፣ የነአርዲ፣ የነስላም መገኛ መሬት የ13 ወራት ፀጋ ያላት ፣ የታላቁ ወንዛችን የግዩን መፍለቂያ የተለያዩ ህዝቦች በልዩነት ውስጥ አንድ ሆነው በፍቅር በሰላምና በመቻቻል የሚኖሩበት ምድር እንደመሆኗ በተለያዩ ጊዜያትም በአለም አቀፍ የተባበሩት መንድታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESO) ውስጥ በተከታታይ የሚዳሰሱና የማይናዳሰሱ ቅርሶችን በማስመዝገብ ከአፍሪካ ቀዳሚ ስፍራን በመያዟ በአያሌ ቱሪስቶች ዘንድ ተመራጭነትን አግኝታለች በብዙሀኑም ትጎበኛለች ከአመት እስከ አመትም እንደ ሚታወቀው የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዕድገት በሚደንቅ ሁኔታ እየጨመረ ይገኛል፡፡ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲም በዚሁ መስክ ተማሪዎችን በመቀበልና በማሰልጠን በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ስር የቱሪዝምና ሆቴል አስተዳዳር የትምህርት ክፍል ከጀመረ 5 አመቱን አስቆጥሯል፡፡ በዚህም አመት ለ3ተኛ ጊዜ  የቱሪዝም አስተዋፅኦ ለሀገር ዕድገት በሚል መሪ ቃል ከታሣሳስ 17-21/2009 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ እንደተከበረ ይገኛል፡፡ 

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የቱሪዝምና ሆቴል አስተዳደር የትምህርት ክፍልም ይህንን ጉልህ አስተዋፅኦ በመረዳት በሙያው የሰለጠኑ ፣ ለሀገር ኢኮኖሚ የበኩላቸውን ሊወጡ የሚችሉ ይልቁንም ደግሞ ብቃት ያላቸው ተማሪዎችን በፅንሰ ሀሣብ ደረጃ ከመስጠት ባለፈ በተግባር እንዲዘጋጁና ለወደፊትም ብቁ፣ ዜጋ በመሆን ለራሳቸውና ለሀገራቸው በቱሪዝሙ መስክ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡የዘንድሮው MICE ሳምንት ታህሣስ 21 በሚኖረው public lecture ኘሮግራም ፍፃሜውን ያገኛል፡፡

Share