የቀዶ ሕክምና አገልግሎት

የአዲስ ዓመት ብስራት ከጥበበ ግዮን ላዕላይ ሆስፒታል (Tibebe Ghion Specialized Hospital)!

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የጥበበ ግዮን ላዕላይ ሆስፒታል እስራኤል ሀገር ከሚገኘዉ ራቢን ህክምና ማዕከል (Rabin Medical Center) በሊንሰን ሆስፒታል(Belison Hospital) ጋር በመተባበር በስፔሻሊስትና ድኅረ-ስፔሻሊስት ሐኪሞች ከመስከረም 12, 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት (4) ቀናት በሚከተሉት የጤና ችግሮች ማለትም:-
1. የጉሮሮ ካንሰር
2. የጨጓራ ካንሰርና ሌሎች የጨጓራና የአንጀት በሽታዎች/ህመሞች/
3. የሐሞት ጠጠር: የጉበት እጢና ተያያዥ በሽታዎች/ህመሞች/
የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ይሰጣል:: ስለሆነም ችግሩ ያለባችሁ ሰዎች ወደ ሆስፒታላችን በመምጣት ከመስከረም 7-9 ባሉት የስራ ቀናት ቅድመ ምርመራ በማድረግና ለቀዶ ህክምና ተራ (ወረፋ) በመያዝ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪዉን ያቀርባል::

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University