መልካም ዜና!!!

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የማስፋፊያ መሬት ጥያቄን ተቀብሎ አጸደቀ፡፡

ጥር 14፣ 2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር)፦ የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ/ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የጠየቀዉን የማስፋፊያ መሬት ለመስጠት ወሰነ፡፡

ከተማ አስተዳደሩ የፈቀደዉ ቦታ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ትምህርት ሚንስቴርና ጤና ሚንስቴር ካስቀመጡት ፍኖተካርታ በመነሳት የሕክምና አገልግሎት፣ የመማር ማስተማና የምርምር ጥራትን ለማሻሻልና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም የዋና ዋና ከተሞችን የሕክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ መንግስት ያስቀመጠዉን አቅጣጫ መነሻ በማድረግ ዓለም አቀፍ ደረጃዉን የጠበቀ ከፍተኛ የስፔሻሊቲና ድሕረ ስፔሻሊቲ የሕክምና ማዕከል ማስፋፊያ የሚዉል ነዉ፡፡

በማስፋፊያ ፕሮጀክቱ የድንገተኛ አደገና ቃጠሎ፣የጽኑ ሕሙማን፣የልብና ተዛማጅ ችግሮች፣የኩላሊት እጥበትና ንቅለ-ተከላ፣የጉበትና ተያያዥ ህመሞች፣የካሰርና ማገገሚያ ሕክምና መስጫና ማስተማሪያ ማዕከላት (Multi-specialty and Subspecialty Centers) የሚቋቋሙ ይሆናል፡፡

የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ለክልላችን ብሎም ለሀገራችን የጤና ዘርፍ መሻሻል እጅግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

Follow us on:

Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu/
Website: http://www.bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information-office-CMHS-BDU
Twitter: https://twitter.com/CollegeBdu?s=20

date: 
Saturday, January 22, 2022 - 10:15

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University