ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
BDU
05 Nov, 2025
ቀን፡- 24/02/2018 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ :-
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው በማታው መርሀ-ግብር በአቅም ማሻሻያ (Remedial) መማር ለሚፈልጉ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በትምህርት ሚኒስትር የወጣውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ እስከ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች፣
● የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፤
● ለማመልከቻ የተከፈለበት ደረሰኝ (Application fee 300 ብር)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፦1000224663378
የክፍያ መጠን፦ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች 4,480
ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች 3,720
የማመልከቻ ቦታ፦
● በተከታታይና ርቀት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 በአካል በመቅረብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ