News

Call for Papers

2ተኛው አለም አቀፍ የአዝማሪ አውደጥናት “አዝማሪ ከየት ወደ የት” በሚል መሪ ቃል በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ:: በአዝማሪዎች ግጥም ድርደራና የመሰንቆ ጨዋታ በታጀበው ሥነ-ሥርዓት ላይ ስለ አዝማሪ ቅኝት እና የአዝማሪነት ሙያ፤ እንዲሁም የአዝማሪነት ሙያ የማንነት መገለጫ የሆነውን ባህል ለማስተዋወቅ ያለውን ፋይዳ፣ አዝማሪዎች የሚገጥሟቸው ግጥሞች የርዕስ ጉዳዮች ጥልቀት እና የመሰሳሉ ጥናታዊ ፅሑፎች ቀርበዋል፡፡ 
የአባይ የባህልና ልማት ጥናትና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉቀን አንዷለም እንዳሉት የአውደ ጥናቱ መከበር ዋና ዓላማ በሀገራችን ዘመናትን የተሻገረው የአዝማሪዎች ቅኝት እስካሁን ድረስ የሚገባውን ትኩረት ስላልተሰጠው የተለያዩ ተመራማሪዎችን፣ የሚመለከታቸውን ባለድርሻ... Read More