በ2012 ዓ/ም የነፃ ትምህርት ተጠቃሚ ለመሆን ለሚፈልጉ አመልካቾች

               በ2012 ዓ/ም የነፃ ትምህርት ተጠቃሚ ለመሆን ለሚፈልጉ አመልካቾች

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ/ም በመደበኛ መርሃ ግብር በሚሰጡ የ2ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ባሉት ክፍት ቦታዎች ብቻ ከትምህርት ክፍያ ነፃ ትምህርት እድል የሚሰጥ መሆኑን እየገለጽን የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1ኛ በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት (ከነሐሴ 1 ቀን 2011 ዓ/ም እስከ መስከለም 9 ቀን 2012 ዓ/ም) የማመልከቻ ፎርማሊቲዎችን አሟልቶ መመዝገብ ይኖርጋቸዋል፤

2ኛ በማመልከቻ ወቅት ኢፊሺያል ትራንስክሪፕት (Official Transcript) ለሬጅስትራር ማቅረብ ይኖርበታል፤

3ኛ የመጀመሪያ ድግሪ አማካይ ውጤት 3.50 እና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል፤

4ኛ የመግቢያ ፈተና ወስደው ያለፉ መሆን ይኖርበቸዋል፤ 5ኛ የነፃ ትምህርት ዕድል ለማግኘት ማመልከትና ለነፃ ትምህርት የተዘጋጀውን ፎርም መሙላት ይጠበቅባቸዋል

ማሳሰቢያ፤ የምዝገባ መስፈርቱን አሟልተው የመግቢያ ፈተናዉን ያለፉና የነፃ ትምህርቱን እድል ያገኙ እጩዎች ዩኒቨርስቲው የትምህርት ወጭዉን ብቻ (የምርምር' የምግብ ' የዶርምና የህክም አገልግሎት ወጭን ሳይጨምር) የሚሸፍን መሆኑን ይገልፃል፡፡

የምዝገባ ቦታ፤ጥበብ ህንጻ አካዳሚክስ ጉዳዮች ኤክስኪውቲቭ ዳይሬክተር ቢሮ

deadline: 
Wednesday, August 7, 2019 to Friday, September 20, 2019