You are here

Admission Requirements/የትምህርት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት

የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ

ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት

 

  1.  የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም (መጀመሪያ ዲግሪ) ለመማር የሚያመለክቱ የመግቢያ መስፈርት

1.1 በከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ውጤት ለሚያመለክቱ

1.1.1 (ሀ) ለመደበኛ ፕሮግራም

  • የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው በትምህርት ሚኒስቴር የሚወጣውን የዘመኑን የዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ፤

        (ለ) ለኢ-መደበኛ ፕሮግራም

  • ፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው የዘመኑን የከፍተኛ ትምህርት ለመከታተል የተቀመጠውን ዝቅተኛ የመግቢያ ነጥብ ያሟሉ፤
  • በ2015 ዓ/ም እና በ2016 ዓ/ም ለሁሉም ፆታ 50% እና ከዚያ በላይ (ለተፈጥሮ ሳይንስ 350፤ ለማህበራዊ ሳይንስ 300፤ ለዓይነ ስውራን 250) እና ከዚያ በላይ ያመጡ፤
  • በ2014 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 50% (ለተፈጥሮ ሳይንስ 1ኛ ዙር ተፈታኝ 300፤ 2ኛ ዙር ተፈታኝ 350 እና ለማህበራዊ ሳይንስ 1ኛ ዙር ተፈታኝ 250፤ 2ኛ ዙር ተፈታኝ 300) እና ከዚያ በላይ ያመጡ፤ ለግል (ድጋሚ ተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች) ለሁሉም ፆታ 355 እና ከዚያ በላይ፤
  • በ2013 ዓ.ም ለወንድ 330፤ ለሴት 320 እና ከዚያ በላይ
  • በ2012 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 140 እና ከዚያ በላይ
  • ከ2009 - 2011 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 295 እና ከዚያ በላይ
  • በ2008 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 275 እና ከዚያ በላይ
  • በ2007 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 250 እና ከዚያ በላይ
  • ከ2004 - 2006 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 265 እና ከዚያ በላይ
  • በ2003 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ (ለወንድ 298፤ ለሴት 280)፤ ለማህበራዊ ሳይንስ (ለወንድ 290፤ ለሴት 280) እና ከዚያ በላይ
  • በ2002 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ (ለወንድ 180፤ ለሴት 150)፤ ለማህበራዊ ሳይንስ (ለወንድ 205፤ ለሴት 180) እና ከዚያ በላይ
  • በ2001 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ (ለወንድ 128፤ ለሴት 126)፤ ለማህበራዊ ሳይንስ (ለወንድ 206፤ ለሴት 151) እና ከዚያ በላይ
  • በ2000 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ (ለወንድ 221፤ ለሴት 176)፤ ለማህበራዊ ሳይንስ (ለወንድ 238፤ ለሴት 176) እና ከዚያ በላይ
  • በ1999 ዓ.ም እና በ1997 ዓ/ም ለወንድ 201፤ ለሴት 175 እና ከዚያ በላይ
  • በ1998 ዓ.ም ለወንድ 201 እና ከዚያ በላይ፤ ለሴት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ያስመዘገቡ በሙሉ፤
  • በ1996 ዓ.ም ለሁሉም ፆታ 101 እና ከዚያ በላይ

1.1.2 ከ2001 ዓ/ም ጀምሮ በቀድሞው የትምህርት ፖሊሲ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያነት አያገለግልም፤

1.1.3 በአንድ ዘመን የተቆረጠ የመቁረጫ ነጥብ ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ዓመታት ብቻ በግላቸው ለሚማሩ ያገለግላል፡፡ ከ5 ዓመት በኋላ ስለማይሰራ በግላቸው ከፍለው ለመማር የሚፈልጉ እንደ አዲስ የመግቢያ ፈተና ወስደው በዘመኑ የሚቆረጠውን የመቁረጫ ነጥብ ያመጡ፤

1.1.4 ከ2014 ዓ/ም በፊት በነበሩ የመቁረጫ ነጥብ ይማሩ ለነበሩ/መማር ለሚፈልጉ የየዘመኑ የከፍተኛ ትምህርት የመቁረጫ ነጥብ ያለምንም የጊዜ ገደብ የሚስተናገዱና የ5 ዓመቱ የጊዜ ገደብ አቆጣጠር ለሁሉም አመልካቾች ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

  1. ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በዲኘሎማ ለሚያመለክቱ፤
    1. ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለመግባት፤
  • በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ 10ኛ ክፍልን (በቀድሞው 12ኛ ክፍልን) ስለማጠናቀቃቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
  • ቢያንስ በደረጃ 4 /Level 4/ የሙያ ብቃት ምዘና /COC/ ወስደው ብቁ የሆኑና ጊዜው ያላለፈበት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፤
  • የሙያ ብቃት ምዘና ወስደው ብቁ በሆኑበት ሙያ የሁለት ዓመት ተግባራዊ የስራ ልምድ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
  • የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ካገኙበት ሙያ ጋር ተዛማቸ በሆነ ፕሮግራም መቀጠል የሚችሉ፤
  • የግብርና ባለሙያዎች ከደረጃ 4 /Level 4/ ወይም ከዲፕሎማ COC የብቃት ማረጋገጫ ያላቸውና በተመሳሳይ መስክ መቀጠል የሚችሉ
  • ከዲፕሎማ ለመምህርነት ሙያ የሚሰለጥኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡትን የመግቢያ ፈተና ያለፉና በሰለጠኑበት ሙያ መቀጠል የሚችሉ፤
    1. ኦፊሻል ትራንስክርፕት ቀደም ከተማሩበት ተቋም መማር ወደፈለጉበት ተቋም ማስላክ የሚችሉና ትክክለኛ የሆነ ኦፊሻል ትራንስክርፕት ያላቸው፤

2) PGDT ለመማር የሚያመለክቱ የመግቢያ መስፈርት

  1.  ከታወቀ ተቋም በመምህርነት ሙያ የትምህርት መስኮች ብቻ በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ፤
  2.  በግላቸው ከፍለው መማር የሚችሉ ወይም ስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. ኦፊሻል ትራንስክርፕት ቀደም ከተማሩበት ተቋም መማር ወደፈለጉበት ተቋም ማስላክ የሚችሉና ትክክለኛ የሆነ ኦፊሻል ትራንስክርፕት ያላቸው፤  

3) የድህረ ምረቃ ፕሮግራም (2ኛና 3ኛ ዲግሪ) ለመማር የሚያመለክቱ የመግቢያ መስፈርት

3.1 የድህረ ምረቃ ፕሮግራም ለመመዝገብ፤

3.2 ኦፊሻል ትራንስክርፕት ቀደም ከተማሩበት ተቋም መማር ወደፈለጉበት ተቋም ማስላክ የሚችሉና ትክክለኛ የሆነ ኦፊሻል ትራንስክርፕት ያላቸው፤

ከተለያዩ መስሪያ ቤቶች በዩኒቨርሲቲው ነፃ ትምህርት እድል ተሰጥቷቸው የመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር የሚያመለክቱ

  • ዲፕሎማ ወይም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ደረጃ 4 /Level 4/ ያላቸው፤
  • ቢያንስ በደረጃ 4 /Level 4/ የሙያ ብቃት ምዘና /COC/ ወስደው ብቁ የሆኑና ጊዜው ያላለፈበት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፤
  • የሙያ ብቃት ምዘና ወስደው ብቁ በሆኑበት ሙያ የሁለት ዓመት ተግባራዊ የስራ ልምድ ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
  • የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ካገኙበት ሙያ ጋር ተዛማቸ በሆነ ፕሮግራም መቀጠል የሚችሉ ናቸው፡፡

አባሪ፤

የመግቢያ መስፈርት (ከ1996 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ ላልሆኑ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ መቁጫ ነጥብ)

12ኛ ክፍል የተፈተኑበት ዘመን

ወደ ከፍተኛ ትም/መግቢያ ዘመን

የየዘመኑ መቁረጫ ነጥብ

ምርመራ

ተፈጥሮ ሳይንስ

ማህበራዊ ሳይንስ

   ወንድ

   ሴት

   ወንድ

     ሴት

1995

1996

101

101

101

101

 

1996

1997

201

175

201

175

 

1997

1998

201

ሁሉም

201

ሁሉም

 

1998

1999

201

175

201

175

 

1999

2000

221

176

238

176

 

2000

2001

128

126

206

151

 

2001

2002

180

150

205

180

 

2002

2003

298

280

290

280

ከ500

2003

2004

265

265

265

265

ከ700

2004

2005

265

265

265

265

ከ700

2005

2006

265

265

265

265

ከ700

2006

2007

250

250

250

250

ከ700

2007

2008

275

275

275

275

ከ700

2008

2009

295

295

295

295

ከ700

2009

2010

295

295

295

295

ከ700

2010

2011

295

295

295

295

ከ700

2011

2012

140

140

140

140

ከ400 (Eng., Math., Apt. & Phy./Geo.

2012

2013

330

320

330

320

 

2013

2014 (1ኛ ዙር)

300

300

250

250

ከ600 (ተ/ሳይንስ)፤ ከ500 (ማህ/ሳይንስ) (Civics cancelled)

2014 (2ኛ ዙር)

350

350

300

300

ከ700 (ተ/ሳይንስ)፤ ከ600 (ማህ/ሳይንስ)

2014

2015

350

350

300/250

300/250

ከ700 (ተ/ሳይንስ)፤ ከ600 (ማህ/ሳይንስ)፤ከ500 (ዓይነ ስውራን)

2015

2016

350

350

300/250

300/250

ከ700 (ተ/ሳይንስ)፤ ከ600 (ማህ/ሳይንስ)/ከ500 (ዓይነ ስውራን)

ማሳሰቢያ፤ ከ2014 ዓ/ም ጀምሮ በአንድ ዘመን የተቆረጠ የመቁረጫ ነጥብ ለ5 ተከታታይ ዓመት ብቻ ያገለግላል፡፡ ከ5 ዓመት በኃላ እንደ አዲስ የመግቢያ ፈተና ወስዶ በዘመኑ የሚቆረጠውን የመቁረጫ ነጥብ ማምጣት ይጠበቃል፡፡

 

 

Contact

 

 Main Registrar Office 

Tel:   0582205934

 

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2019- Bahir Dar University