የስራ ሀላፊነት፡ የአቅም ግንባታ ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያ I

የአቅም ግንባታ ከፍተኛ የስልጠና ባለሙያውተጠሪነቱ ለጥራት ማሻሻያ ዩኒት ዳይሬክተር ሆኖ የሚከተሉት ተግባራት ይኖሩታል፡
 
4.1. በዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የስራ ክፍሎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ያለውን የስልጠና ፍላጎት ያጠናል፣
4.2. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ስለስልጠናውን አይነት፣ የስልጠና ጊዜና የሰልጣኞች ብዛት መረጃ ይሰበስባል፣
4.3. ከሚመለከታቸው ክፍሎች የአሰልጣኝ ጥቆማ ይቀበላል፣
4.4. የተሰበሰቡ የስልጠና ፍላጎቶች፣ የስልጠና አይነትና ጊዜ መረጃዎችን አቀናብሮ ለጥራት ማሻሻያ ጽ/ቤቱ ያቀርባል፣
4.5. ስልጠናው በታቀደለት ጊዜ እንዲካሄድ አስፈላጊውን ግብዓት ለማሟላት ከቅርብ ሀላፊዎች ጋር መስራት፣በስልጠና ወቅት ስልጠናዎች በአግባቡ እንዲካሄዱ ያስተባብራል፣
4.6. ከስልጠናዎች በኋላ ስለስልጠናዎች አጠቃላይ አስተያየቶችን ይሰበስባል፣
4.7. ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን ቁም ነገር በስራቸው ላይ በምን መልክ እየተጠቀሙበት እንደሆነ ይዳስሳል፣
4.8. በዳሰሳው የተገኘውን ውጤት ለምክትል ዳይሬክተሩ ሪፖርት ያደርጋል፣
 
4.9. ከተሰጠው ሀላፊነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሌሎች ተጨማሪ ተግባራት ያከናውናል፡፡