የውስጥ የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

ጥር 23/2011 ዓ.ም

 

የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጥናቶች ተቋም ምክትል ዲን /ዳይሬክተር የነበሩት የስራ ጊዜያቸውን ስላጠናቀቁ በምትካቸው በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መሾም ይፈልጋል፡፡

 

የማወዳደሪያ መስፈርት

1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት

2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤

3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

 

አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሰቲው ድህረ-ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት ከጥር 23/2011 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሰቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡ + 251 58 226 32 10 ወይም + 251 918 35 34 94 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡