የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ በዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ላይ ውሳኔ ሰጠ

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ዛሬ ታህሳስ 2 ቀን 2010 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በቅርቡ ሲካሄድ በቆየው የዩኒቨርሲቲው የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውድድር ተወዳዳሪዎች ያስመዘገቧቸውን ውጤቶች በተመለከተ በስፋት ከተወያየ በኋላ ከተወዳዳሪዎች ውስጥ፡

  • ዶ/ር ፍሬው ተገኘ አሞኘን፣

  • ዶ/ር ማተቤ ታፈረ ገድፈውን እና

  • ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ አለባቸውን

መርጦ ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ያቀረበ ሲሆን በነዚሁ መመዘኛዎች አጠቃላይ ድምር በአንደኛ ደረጃ የወጡት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ አሞኘ የዩኒቨርሲቲው ቀጣይ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ለትምህርት ሚኒስቴር ምክረ ሀሳብ አቅርቧል፡፡

የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ከትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዚዳንት አወዳድሮ የሚመርጥ አንድ ቡድን በመሰየምና አመልካቾችን በመጋበዝ ተወዳዳሪዎቹ በተለያዩ መመዘኛዎች እንዲወዳደሩ ሲያደርግ የቆየ ሲሆን በምርጫ ሂደቱም የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ ማሳተፉ ይታወሳል፡፡