ለመምህራን የመጀመርያ ዙር የLMS Training ተሰጠ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲዉ የአይ.ሲ.ቲ. ዳይሬክቶሬት እና ከአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ተመራቂ ተማሪዎችን ለሚያስተምሩ ቅድሚያ በመስጠት ከጥቅምት11-24/2013 ዓ/ም በሁሉም ግቢ ለሚገኙ መምህራን የLearning Management System ( LMS ) ስልጠና ሰጥቷል ፡፡

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬት አቶ ወርቁ አበበ እንደተናገሩት በዩኒቨርሲቲው የሚካሄደውን የመማር ማስተማር ሂደት በICT በመደገፍ የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ከኢፌዲሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት በCovid 19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስቀጠል እና ተማሪዎችን ለመቀበል የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ሲያደርግ መቆየቱ የሚታወቅ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡ በዚህም መሰረት በመጀመርያዉ ዙር 206 መምህራን ስልጠናዉን የወሰዱ ሲሆን ተሳታፊዎችም በሰለጠኑት አግባብ የሚያስተምሩበትን የትምህርት መሳሪያ ሲስተም ላይ ማስቀመጥ ችለዋል፡፡ ይህ በመሆኑም ተማሪዎች ትምህርት ሲጀምሩ የተቀመጠላቸውን የተለያዩ የትምህርት መሳሪያዎች በየትኛዉም ቦታ ሆነዉ ማግኘት እና መጠቀም እንዲችሉ የሚያግዛቸዉ መሆኑ ተገልፆል ፡፡

 

በቀጣይም ለሌሎች መምህራን እና ለተማሪዎች ስልጠናዉ እንደሚቀጥል ማወቅ ተችሏል፡፡