የሥልጠና ጥሪ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አጋር የኾነው ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ሲንሲናቲ ልዩ፣ልዩ የበይነመረብ ፕሮግራሞችን አዘጋጅቷል፡፡ ከነዚህ ፕሮግራሞች መካከል ግሎባል ባክ ቢዝነስ  የተሰኘ ሥልጠና ዩኒቨርሲቲያችንን ጨምሮ ከአጋር ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መስጠት ይፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ አጋር ዩኒቨርሲቲ አምስት ሰልጣኞችን ማሳተፍ የሚችል ሲኾን፣ ሰልጣኞች ቢያንስ አምስት ዓመት በ(ንግድ) ሥራ የተሰማሩና ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው እንዲኾኑ ይጠበቃል፡፡ አመልካቾች አጭር ሲቪና ለሥልጠናው ያላቸውን ተነሳሽነት በአንድ ገጽ ለ Tilahun.Bejtual@bdu.edu.et  እስከ  ሴፕቴምበር 28 (መስከረም 18 2013 ..) ድረስ ብቻ  መላክ ይኖርባቸዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ የሥልጠና ጥሪውን ፖስተር ይመልከቱ፡፡

Friday, September 4, 2020 - 12