የውስጥ የስራ ማስታወቂያ (በድጋሚ የወጣ)- ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ

ቀን፡ 15/12/2012 ዓ.ም

የውስጥ የስራ ማስታወቂያ (በድጋሚ የወጣ)

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን ከዩኒቨርሰቲው አወዳድሮ ለቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ  የአካዳሚክ ዲን ለመቅጠር ባወጣው ማስታወቂያ የአመልካቾች ቁጥር በቂ ባለመሆኑ  ማስታወቂያውን በድጋሚ ማውጣት አስፈልጓል፡፡

 የማወዳደሪያ መስፈርት

1ኛ. የትምህርት ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት

2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤

3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

 አመልካቾች፡-

ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሰቲው የማስታወቂያ ሰሌዳና ድህረ-ገጽ ከተገለጸበት ከነሀሴ 15/2012 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ ቀናት የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡