የ 2012 የትምህርት ዘመን ሰላማዊና ውጤታማ ለማድረግ ከተማሪዎች ጋር ውይይት ተደረገ

የ 2012 የትምህርት ዘመንን ሰላማዊና ውጣታማ ለማድረግ ከ2ኛና 3ተኛ አመት የፋኩሊቲው ተማሪዎች ጋር  በዩንቨርስቲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ  ውይይት ተደርጓል፡፡ ውይይቱ የተካሄደው ረቡዕ (05/02/2012) ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ ሲሆን፤ በውይይት ላይ የተገኙት የፋካለቲው ዲን እና ምክትል ዲን ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በተላከው በሰላማዊ የመማር ማስተማር ሰነድ አና በተማሪዎች የዲስፕሊን መመሪያ ላይ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን  ከተማሪዎች ለቀረቡ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷል ፡፡

 

Share