የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የድል መታሰቢያ

የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች የድል መታሰቢያ በዓልን በየአመቱ ሚያዚያ 27 ያከብራል፡፡ በዚህም ዓመት ትምህርት ክፍሉ 78ኛውን የድል መታሰቢያ በዓል በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ዝግጂቱን አጠናቋል፡፡ በዕለቱ ከጊወርጊስ አደባባይ በመነሳት ከ 2:00 ጀምሮ ሰልፍ ይደረጋል፡፡
ስለሆነም ሁሉም  የፋኩሊቲያችን መምህራን እና ፍላጎት ያላቸው አካላት እሁድ ሚያዚያ 27/2011 ዓ.ም በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ 2:30 ላይ በመገኘት የበዓሉ ተሳታፊ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል፡፡ 
 

Date: 
Sat, 05/04/2019
Image: 
Place: 
Bahir Dar University
Share