የፋኩልቲው ተማሪዎች በጀርመን ሀገር ከሚገኘው ሀምቡርግ ዩኒቨርሲቲ ከመጡ ምሁር ጋር ውይይት አደረጉ

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች እና ስነጽሑፍ አማርኛ ትምህርት ክፍል ተማሪዎች እና የፎክሎር ትምህርት ክፍል የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው በእንግድነት ተጋብዘው ከሀምቡርግ ዩኒቨርስቲ ከመጡት ዶ/ር ጌቴ ገላዬ ጋር ውይይት አደረጉ፡፡ ዶ/ር ጌቴ ገላዬ በሀምቡርግ ዩኒቨርስቲ የእስያና የአፍሪካ ጥናት ተቋም መምህርና ተመራማሪ ሲሆኑ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች፣ የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት በጀርመን ዩኒቨርሲቲዎች፣ በአማርኛና ግዕዝ ቋንቋዎች ዙሪያ ጥናትና ምርምር ያደረጉ አውሮፓውያንና ስራዎቻቸው፣አውሮፓውያን ስለምን በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህል ዙሪያ ጥናትና ምርምር ያደርጋሉ፣በተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ሀብቶች አጠባበቅ የወጣቱ ሚና ምን መሆን አለበት፣ በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ባህል ጥናትን አስመልክቶ ሊደረጉ የሚገባቸው ጥናትና ምርምሮች በተመለከተ እና መሰል ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ሀሳቦችን ካቀረቡ በኌላ ከመምህራንና ከተማሪዎች ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በመጨረሻም በውይይቱ የተሳተፉ መምህራንና ተማሪዎች እንዲሁም ዶ/ር ጌቴ ገላዬ ከውይይቱ በርካታ ጠቃሚ መረጃዎችን እንዳገኙ ገልፀዋል፡፡

Share