የስራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል በ2010 ዓ.ም ለሚመረቁ ተማሪዎች የኢንትረፕርነርሽፕ ስልጠና ተሰጠ

የስራ ፈጠራ ልማትና ማበልጸጊያ ማዕከል(Entrepreneurship Development and incubation Center, EDIC) በ2010 ዓ.ም ለሚመረቁ ተማሪዎች የኢንትረፕርነርሽፕ ስልጠና ከኢዲሲ ኢትዮጵያ(EDC,Ethiopia) ጋር በመተባበር ስልጠና ሰጠ፡፡

ማዕከሉ በሶስት የስልጠና አዳራሾች ማለትም በዋናው ግቢ፤በባህር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንቲቱትና በሰላም ካምፓስ ለ1094(ለአንድ ሺህ ዘጠና አራት) ተመራቂ ተማሪዎች ጥቅምት 3 እና 4/2010 ዓ.ም የሁለት ቀን ስልጠና የተሰጠ ሲሆን፡ አንድ ተማሪ ተመርቆ ስራ ከመፈለግ ይልቅ በራሱ ስራ መፍጠር እንዲችል የሚያነቃቃ ነበር፡፡

ስልጠናው የተሰጠው ጠንካራ የማሰልጠን ልምድ ባላቸው የኢዲሲ ኢትዮጵያ አሰልጣኞች ሲሆን ዋና ትኩረቱም፡- የቢዝነስ ሰዎች ሊኖራቸው የሚገቡ ክህሎቶችና እውቀቶች ምን ምን እንደሆኑና ማንኛውም ሰው ሰፋ አድርጎ ማሰብና ማንሰላሰል ከቻለ ከተቀጣሪንት ይልቅ ቢዝነስ መስራት ከፍተኛ ጥቅም እንደሚያሰገኝ በተግባራዊ ምሳሌ በመደገፍ ስልጠናው ተስጥቷል፡፡