ዩኒቨርሲቲው እውቅና ሰጠ

ዩኒቨርሲቲው ለነባር የከፍተኛ አመራር አባላት እውቅና ሰጠ

---------------------------------------------------------

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ኃላፊነታቸውን በማጠናቀቃቸው ሙሉ በሙሉ ግልጽ በሆነ ውድድር በአዲስ የተተኩ ነባር የከፍተኛ አመራር አባላትን እውቅና ሰጠ፡፡

 

በዩኒቨርሲቲው የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት በተዘጋጀውና በአዲስ የተተኩ አመራሮችን ለማመስገን በተዘጋጀው በዚህ የእውቅና አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ነባሮቹ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተሮችና የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ሀላፊው በስራ ዘመናቸው ዩኒቨርሲቲውን የምርምር ዩኒቨርሲቲ ለማድረግ በሚደረጉት ጥረቶች ውስጥ ላበረከቷቸው አስተዋጽኦዎች የምስጋና የምስክር ወረቀት ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ተቀብለዋል፡፡

 

ለነዚህ ነባር የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር አባላት ምስጋና በተዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ ነባሮቹ አመራሮች ለአዲሶቹ የስራ ርክክብ እና በሃላፊነት ዘመናቸው የጀመሯቸውን ስራዎች እንዲያስቀጥሉ አደራ በማለት የዩኒቨርሲቲውን የጥበብ ሰንደቅ ዓላማና ከእንጨት የተሰራ የጥበብ አርማ ዋንጫ (Wisdom Wooden Trophy) አበርክተውላቸዋል፡፡

 

ዝግጅቱን አስመልክተው ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ዩኒቨርሲቲው በሌሎች ተቋማት ከተወደሰውና ነጻና ግልጽ ውድድርን መርህ ባደረገ መልኩ አመራሮቹን ለመተካት እየተሰራ ከለው ውጤታማ ስራ ጎን ለጎን እየተካሄደ ያለው የሰራን ሰው የማመስገን ባህል በአርዓያነት የሚወሰድ መሆኑን ጠቅሰው ቀጥሎ ባሉት መካከለኛ አመራሮች ደረጃም ይህ ጉዳይ ተጠናክሮ መተግበር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡