የግጥም መድብል ምረቃ

                          ‹‹ስላንች›› የሚል የግጥም መድብል ለንባብ በቃ

 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ-ፅሁፍ ትምህርት ክፍል ተማሪ በሆነው ጌጡ ሳይህ የተፃፈው ‹‹ስላንች›› በሚል ርዕስ የተሰየመው የግጥም መድብል ነሀሴ 19/ 2011 ዓ.ም. በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተመርቆ ለንባብ በቃ ፡፡

በመፅሀፉ ምረቃ ወቅት በጋዜጠኛ ብሩክ ለገሰ የመነሻ ፅሁፍ የቀረበ ሲሆን አጠቃላይ ዳሰሳ እና ሙያዊ አስተያየት በማቅረብ ደራሲው በህይወቱ የታዘባቸውን ፣ የተመለከታቸውን ፣ እንዲሆኑለት የሚመኛቸውን ትዝብቶችን ማካተቱ ተገልጿል ፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ-ፅሁፍ ትምህርት ክፍል መምህርት የሆኑት ወ/ሮ ሂሩት አድማሱን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት ታድመዋል፡፡