የቦርድ አመራር እና ከፍተኛ አመራሮች ችግኝ ተከሉ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራር እና ከፍተኛ አመራሮች ችግኝ ተከሉ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባላት ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር አባላት ጋር በመሆን በአዲሱ የቴክኖሎጂ ቤተ መጽሃፍት ግቢ በተዘጋጀው ቦታ አገር በቀል ችግኞችን  ተከሉ፡፡

በችግኝ ተከላው የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትርና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ኢንጅኔር ስለሺ በቀለ፣  የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ፣ ሌሎች የቦርድ አባላት እና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈውበታል፡፡ ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ከፍተኛ አመራሮች ያደረጉት አርኣያነት ያለው ተግባር መሆኑን ጠቁመው ሌሎች አካላትም ይህን ተከትለው የበለጠ እንዲሰሩ ማሳያ እንደሚሆን እምነታችው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ እስካሁን ባለው የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ከ36000 በላይ የሚሆን ችግኝ በሰባት አሚት፣ በቤዛዊት ተራራና በሌሎች ቦታዎች በዩኒቨርሲቲው መተከሉን ፕሬዚደንቱ ጨምረው አመልክተዋል፡፡