የባሕር ዳር ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች ከተማሪዎች ጋር ተወያዩ

የባሕር ዳር ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች ከተማሪዎች ጋር ተወያዩ

የባህር ዳር ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች እና የዩኒቨርሲቲው አመራሮች  በተማሪዎች የመመገቢያ አዳራሽ በመገኘት ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር ምሳ እየተመገቡ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚታየውን አለመረጋጋት  አስመልክቶ  አባታዊ ምክርና ውይይት አደረጉ፡፡

በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የሚሰማው ችግር በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲም እንዳይከሰትና አሁን ያለውን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሁኔታ በዘላቂነት ለማስቀጠል ተማሪዎችና የባህር ዳር ከተማ የሀገር ሽማግሌዎች በጋራ በመሆን በሰላም ዙሪያ ምክክር  አድርገዋል፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያ አሁን ካለባት የህልውና ስጋት በዘላቂነት ለመውጣት ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ሙሉ በሙሉ ለሰላም መስራት እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡ ተማሪዎችም የባህር ዳር ከተማ ወጣቶችንና ማህበረሰቡን አመስግነው እስካሁን ምንም የተከሰተ ችግር እንደሌለ ጠቅሰዋል፤ ነገር ግን በመካከላቸው የተለዬ አላማ ያላቸው ተማሪዎች አንዳሉ ስጋታቸውን ጠቅሰው እነዚህን ተማሪዎች በማጋለጥና ከእኩይ ተግባራቸው እንዲታረሙ ለማድረግ  ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር በመሆን እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎች አክለውም በሌሎች የሀገራችን ዩኒቨርሲቲዎች ያለውን ችግር የሚመለከታቸው አካላት ሰላምን ከማስጠበቅ አንፃር በትጋት መስራትና ወንጀለኞችን ለፍርድ ማቅረብ እንዳለበቸው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አሳስበዋል፡፡