የመጽሃፍ ምረቃ

ስለመፅሐፉ ይዘቶች በጥቅሉ፡-

በመጽሐፉ የተነሱት ሀሳቦች በጥቅሉ ‹‹ ስለአራቱ የሰው ልጅ መሰረታዊ መጠይቃት (4ቱ የግዕዝ ማንጠሪያዎች) የተሰኙ ጥያቄዎች፣ ስለ ሰውነትና ስነ-ፍጥረት፣ ስለማንነትና ኢትዮጵያዊነት፣ ኢትዮጵያና የታሪኳ ግንድ ፍሰት (የ‹‹7510 ዓመት›› አዛውንት ስለመሆኗ)፣ ስለ የሰው ልጆች ምድራዊ ህይወትናአሰፋፈር(የአዳምና ኖህ ትክክለኛ መኖሪያና የመብዛት ጉዳይ)፣ በዚህች ዓለም ታሪክ ውስጥ ታላቅ ሽሚያ ስለሚደረግበት ‹‹የኖህና ቤተሰቡ የመጀመሪያ ማረፊያና ስለዚህ ቤተሰብ መብዛት ብሎም ርስት የመከፋፈል ጉዳይ››፣ ስለ ገነትና ትክክለኛ መገኛዋ፣ ስለ ‹‹አወዛጋቢው የመልከፄዴቅ ማንነትና ኢትዮጵያ ብሎምእስራኤል››፣ ስለቋንቋና የመጀመሪያው የሰው ልጆች ቋንቋ ውዝግብ (ሱባ ወይስ ግዕዝ)፣ ስለ‹‹የብሄር ፅንሰ-ሃሳብ››፣ ስለ‹‹የኖህ ታሪክ፣ ቅድመ-ኖህ፣ ድህረ-ኖህ፣ ኖህና ኢትዮጵያ፣ ጎንደር ውስጥ የታፈነው ረጅሙ የኢትዮጵያ ታሪክ ማህደር፣ ሰሎሞናዊነትና ኢትዮጵያዊው ዘር ላይ ስለፈፀመው ደባና የክህደት ቁልቁለትመጀመር ሚስጥር፣ ስለ‹‹የመንፈሱ(666) ሴራ፣ የኢትዮጵያ ቅድስናና ሚስጥራዊት ሀገር መሆን፣ የማያውቋት ዜጎች የሚኖሩባት ብቸኛዋ የምድራችን ሀገር-ኢትዮጵያና አሳዛኙ ሀቅ፣ የግዮን ነገር፣ የረርና ሚስጥሩ፣ የመንፈሱ(666) ሴራ ከጥንት እስካሁን ብሎም መደምደሚያው ስለሆነው የብሄር-ዘውግ ሴራው(ስለሀሳዊው ህብረ-ብሄራዊነትና የክሽፈቱ ሚስጥር)፣ ስለ የኢትዮጵያ የኢካቦድ ዘመንና መፈፀሙ፤ ስለኢትጵያ ትንሳኤ . . . ስለ ልዕልናና ትምህርት በኢትዮጵያ ብሎም አፍሪካ፣ ስለአዲሱና የትንሳኤውን ማንነት መገንቢያ ፍልስፍና (የምሉዕ ሰብዓዊ እድገት ፍልስፍና)፣ የኢትዮጵያ ሁለገብ- ክሽፈት ዋና መሰረትስለሆነው ‹‹ግንጥል-ልዕልና››፣ በኢትዮጵያ ስነ-አስተምህሮዎችና የዘመን አቆጣጠር ላይ ስለተደረጉ ሴራዎችና ስለመንቃት፣ ስለ ቤተ-ክነትና ቤተ-መንግስት ክሽፈት፣ ስለ ቤተ-ህዝብ ባይተዋርነት፤ ስለ ትክክለኛው የምድራዊ ህይወት ዘይቤና ብሎም አዲስ ኢትዮጵያዊ አርድኦትና ብሂሎቹ፣ ስለሳትንባቸው አብይአስተሳሰቦች . . . . ወዘተ . . . አብይ ርዕሶች የሚነገሩና የሚያወዛግቡ ጉዳዮችና ሀሳቦች ሁሉ . . . በመጽሐፉ የተነሱ ሲሆን፤ . . . ደራሲው፡ እነኝህን ሁሉ ሀሳቦች በሚያነሳበት ዑደት ውስጥ፡ ‹‹ኢትዮጵያ ታላቅ ትንሳዔ ከፊት ለፊቷ የሚጠብቃት ድንቅ ሀገር ነችና አይዟችሁ፤ ሆኖም ግን ሀገሪቷን በደንብ ልናውቃትና ልንረዳት ብሎም ለዚህች ድንቅ ሀገር የሚሆን ላቅ ያለ ሁለንተናዊ የስብዕና እድገትን ማምጣት የሚሻን መሆኑን ተገንዝባችሁ፡ ለዚሁ ተዘጋጁ፣ ንቁም›› ሲል በተስፋ ሀይል እየሞላና ስለመነሳት አቤት በማለት ነው፡፡ ››››› በበለጠ በምረቃ መርሀ-ግብሩ ላይ በመገኘትና መጽሐፉን በማንበብ ሀሳቦችን ማዳበር የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፡ በድጋሜ የመርሀ-ግብሩ ተሳታፊ እንድትሆኑ እናሳስባለን፡፡ 

ዩኒቨርሲቲው
Wednesday, February 20, 2019 - 21