የህይወት ክህሎት ስልጠና

ለተመራቂዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና እየተሰጠ ነው
-----------------------------------------------------
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውጤታማ ትግበራ ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው የስልጠና ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር Cover letter writing, CV writing፣ Mock interview , Self confidence and Interpersonal communication በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ የክህሎት ስልጠና እየሰጠ ነው ፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የውጤታማ ትግበራ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ጴጥሮስ ክበበው ስልጠናውን ሲሰጡ እንደተናገሩት በተለይ በዘንድሮ አመት ILO (International labor organization) ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በተፈራረሙት መሰረት፤ ከትምህርት እና ስነ ባህሪ ኮሌጅ ለተመረጡ መምህራን ስልጠና እንዲሰጥ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ባሁኑ ስዓት በ10 የዩኒቨርሲቲ ሥልጡን መምህራን አማካኝነት ለBIT፣ IoTex እና ይባብ ግቢ የዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ስልጠናው የተሰጠ ሲሆን በቀጣይም በሁሉም ግቢዎች ቅዳሜ እና እሁድ ስልጠናው እንደሚቀጥል ገልፀዋል ፡፡

አቶ ጴጥሮስ አክለውም ተመራቂ ተማሪዎች ገበያው የሚፈልገውን እውቀት፣ ክህሎት እና አመለካከት ጨብጠው ይወጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የአሁኑ የህይወት ክህሎት ስልጠና ደግሞ እራሳቸውን ብቁ እና ተፎካካሪ አድርገው ለመቅረብ ያስችላቸዋል ብለዋል ፡፡