ዓውደ ጥናትና የመስክ ጉብኝት ተካሄደ

በሙሉጎጃም አንዱዓለም

በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ስር የሚገኘው Development of Micro grid Research Center in Bdu to Support USAID’S Power Program የተሰኘው ፕሮጀክት በጃካራንዳ ሆቴል ዓውደ-ጥናት፣ በወራሚት ቀበሌ ደግሞ የመስክ ጉብኝት አካሄደ፡፡

መርሃ- ግብሩ በይፋ መጀመሩን ያበሰሩት የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሰይፉ አድማሱ ለታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ዓውደ ጥናቱ  ፕሮጀክቱ ለሚያከናውናቸው የተለያዩ ተግባራት ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው ያላቸውን እምነት ገልፀው ፍሬያማ ውይይት እንዲሆን ተመኝዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ መምህርና የፕሮጀክቱ ዋና ተመራማሪ ዶ/ር በላቸው ባንትይርጋ በንግግራቸው እንደጠቀሱት ፕሮጀክቱ ታዳሽ ሀይሉችን በመጠቀም የተለያዩ ፋና ወጊ ተግባራትን እያከናወነ እንደሆነ ገልፀው ለአብነትም በወራሚት ቀበሌ የሚገኘውን ት/ቤት በሶላር አማካኝነት የመብራት ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

በፕሮግራሙ  የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዘዳንት ዶ/ር ፍሮው ተገኘን ጨምሮ የተለያዩ ምሁራን የታደሙ ሲሆን በወራሚት ቀበሌ ሉማሜ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ የተሰራውን “የማክሮግሪድ” ሰርቶ ማሳያ ጣቢያ በመስክ ጉብኝቱ ለማየት ተችሏል፡፡