ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ

በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የግልና የመንግስት ተቋማት የጤና ስፖርት ቡድኖች መካከል በበርካታ ዙሮች ሲካሄድ የነበረው ውድድር ተጠናቀቀ።

በውድድሩም የእግር ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ የቼዝና የጠረንጴዛ ቴንስ  ስፖርቶች  ፉክክር የተደረገ ሲሆን ሲሆን የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የጤና ስፖርት ቡድናችን በእግር ኳስና በመረብ ኳስ የፍጻሜ ጨዋታዎች የዋንጫ ባለቤት ሆኗል፡፡ በሁለቱም የውድድር መስኮች ኮከብ ተጫዋችና አሰልጣኝ ሆነው የተመረጡትም ከዚሁ ከዩኒቨርሲቲያችን የጤና ስፖርት ቡድን ሲሆን በመረብ ኳስ ኮከብ ተጫዋች ኢንስፔክተር አለማየሁ ተፈራ፣ ኮከብ አሰለጣኝ ደግሞ መምህር ዘመኑ ተሾመ ሲሆኑ በእግር ኳስ ደግሞ ኮከብ ተጫዋች የሆነው ዳንኤል ጌትነት ሲሆን ኮከብ አሰልጣኝም ሞክሸው ዳንኤል ጌትነት ሆነዋል፡፡ ለኮከብ ተጫዋችና ኮከብ አሰልጣኞችም  የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

 የባሕር ዳር ቴክኖሎጅ ኢንስትቲዮት እግር ኳስ ቡድን የውድድሩ የጠባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል። ውድድሩን በአሸናፊነት በመወጣት ዋንጫ የወሰዱት ሁለቱ ቡድኖች በቀጣይ በአማራ ክልል የጤና ቡድኖች ውድድር ላይ ከተማ አስተዳደሩን ወክለው የሚሳተፉ ይሆናል። በተያያዘ ዜናም የጠረጴዛ ቴንስ ቡድናችን ሁለተኛ በመሆን የብር ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል፡፡

በውድድሩ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኘን ጨምሮ ሁሉም ም/ፕሬዚደንቶች ተገኝተው ጨዋታዎቸን የተከታተሉ ሲሆን በእለቱ  ተሸላሚ ለሆኑትም ዶክተር ፍሬው ተገኘ የዋንጫ ሽልማት አበርክተዋል፡፡