ሴት ተማሪዎች ስልጠና

ለሴት ተማሪዎች ስልጠና ተሰጠ
**************************
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስልጠና ዳይሬክተር ከዩኒቨርሲቲው ስርዓተ ፆታ ጋር በመተባበር ከተለያዩ ግቢዎች ለተመረጡ ሴት ተማሪዎች የምክክርና ክትትል (mentorship) ስልጠና ከቅዳሜ ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ንግግር ያደረጉት በዩኒቨርሲቲው የስልጠና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ወርቁ አበበ ሰልጣኞች ስልጠናውን ከወሰዱ በኃላ ወደ ኮሌጅ በመሄድ በአካዳሚክ ዘርፍም ሆነ በማህበራዊ ሁነቶች ላይ የምክር አገልግሎት በመስጠት እንደ ታላቅ እህት ሆነው የታላቅ እህትነት ድርሻቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ብለዋል ፡፡