BDU (LSCM), KUEHNE-STIFTUNG Signed MOU

ሎጅስቲክስ እና ሰፕላይ ቼይን ማናጅመንት ት/ት ክፍል ከKUEHNE-STIFTUNG ፋውንዴሽን  ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

በባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የሎጅስቲክስ እና ሰፕላይ ቼይን ማናጅመንት ት/ት ክፍል ከKUEHNE-STIFTUNG ፋውንዴሽን ጋር የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

በስምምነቱ ላይ እንደተገለፀው ሁለቱም ወገኖች ሎጅስቲክስ እና ሰፕላይ ቼይን ማናጅመንት ሙያን ለማሳደግ በትምህርት፤ በምርምር እና በመሳሰሉት ላይ በጋራ ለመስራት ያስችላቸዋል፡፡

ይህም የትምህርት ክፍሉን መምህራኖች እና ተማሪዎች ከሌሎች አገሮች ልምድ የሚያገኙበት እንደመሆኑ መጠን የትምህርት ጥራትን፤ በሎጅስቲክስ እና ሰፕላይ ቼይን ማናጅመንት ዘርፍ የተለያዩ ምርምሮችን ለመስራት አጋዥ እንደሚሆንም ተጠቁሟል፡፡

Share