በየሳምንቱ አቮካዶ መመገብ የልብ ሕመም አደጋን ሊቀንስ ይችላል።

(ሚያዚያ 08፣2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር)፦ በየሳምንቱ አቮካዶ የሚበሉ ሰዎች አቮካዶ እምብዛም ከማይመገቡ ሰዎች ጋር ሲወዳደር ለልብ እና የደም ቧንቧ በሽታ የመጋለጥ እድላቸውን ሊቀንስ ይችላል ሲል በሃርቫርድ ቲ.ኤች የቻን የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት (HARVARD T.H Chan School of Public Health) ተመራማሪዎች የተመራው አዲስ ጥናት አመልክቷል።

ተመራማሪዎቹ እንደ ቅቤ፣ አይብ ወይም የተቀነባበረ ስጋን የመሳሰሉ የእንስሳት ተዋፅኦዎችን በተመጣጣኝ መጠን በአቮካዶ መተካት የልብና የደም ሥር (cardiovascular) በሽታዎች የመከሰት እድላቸው ዝቅተኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ጥናቱ መጋቢት 22፣ 2014 ዓ.ም በጆርናል ኦፍ ዘ አሜሪካን የልብ ማህበር (Journal of the American Heart Association) ላይ ታትሟል።

ተመራማሪዎቹ በነርሶች የጤና ጥናት እና በጤና ባለሙያዎች ክትትል ጥናት ውስጥ ከ110,000 በላይ ሴት እና ወንድ ተሳታፊዎች የ30 ዓመታት መረጃን ተመልክተዋል። የተለያዩ የልብና የደም ሥር ነክ ጉዳዮችን እና አጠቃላይ የአመጋገብ ስርዓትን ከግምት ውስጥ ካስገቡ በኋላ በጥናቱ ወቅት ቢያንስ በሳምንት ሁለት ጊዜ ግማሽ አቮካዶ የበሉ ሰዎች የልብ በሽታ የመጋለጥ እድላቸው 16 በመቶ ዝቅተኛ እና የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸዉ 21 በመቶ ዝቅተኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በጥናቱ ወቅት በቀን ግማሹን የእንስሳት ተዋፅኦን አመጋገባቸዉን በአቮካዶ የተኩ ሰዎች የልብና የደም ቧንቧ በሽታዎች የመጋለጥ እድላቸው ከ16-22 በመቶ ቀንሷል።

"እንደ አይብ እና የስጋ ያሉ የተወሰኑ ግባቶችን እና ቅባት የያዙ ምግቦችን በአቦካዶ መተካት ሀኪሞች እና ሌሎች የጤና እንክብካቤ ባለሙያዎች ማለትም የተረጋገጠላቸዉ የስ-ምግብ ባለሙያዎች ከታካሚዎች ጋር ሲገናኙ ሊያደርጉት የሚችሉት ነገር ነው፤በተለይ አቮካዶ ጥሩ በደንብ ተቀባይነት ያለዉ ምግብ ስለሆነ።” ሲሉ መሪ ደራሲ ሎሬና ፓቼኮ፣ በሃርቫርድ ቻን ትምህርት ቤት የስነ-ምግብ ዲፓርትመንት የድህረዶክትሬት (Postdoctoral) ጥናት ባልደረባ በዜና መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!

Follow us on:

Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu/
Website: http://www.bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information-office-CMHS-BDU
Twitter: https://twitter.com/CollegeBdu?s=20

date: 
Saturday, April 16, 2022 - 03:00

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University