የተማሪዎቻችን እንቁ ተግባር!!!

(መጋቢት 3፣ 2014 ዓ.ም፣ባሕር ዳር)፦በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሁለተኛ ድግሪ ተማሪዎች የአካባቢውን ማህበረሰብ በማስተባበር በአንዳሳ የፀበል ተቋም የደረቅ ቆሻሻ ማቃጠያ ገንብተዋል።

የፀበል ቦታው በርካታ ህዝብ የሚስተናገድበት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ይከሰት የነበረውን አላስፈላጊ እና ለጤና ጠንቅ ደረቅ ቆሻሻ በማቃጠል አካባቢውን ፅዱ እና ጤናማ ለማድረግ በእጅጉ እንደሚያግዝ ይታመናል።

የስርዓተ-ትምህርቱ አንድ አካል የሆነው የልማት ቡድን ስልጠና ፕሮግራም ( Development Team Training Program (DTTP)) ተማሪዎች የአካባቢውን ችግር በማጥናት እና አንገብጋቢ የሆኑትን በመለየት እና የተለዩትን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ችግሮች ለመቅረፍ ፕሮጀክት በመቅረፅ ማህበረሰቡን በማስተባበር የሚተገበር ፕሮግራም ነው።

በፕሮግራሙም በርካታ የማህበረሰቡን ችግሮች በተግባር ከመቅረፍ ባለፈ ተማሪዎቹ ከምንም በላይ የሀገራቸውን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች እንዴት ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መለየት፤የተለዩትን ችግሮች ለመቅረፍ የሚያስችል ፕሮጀክት መንደፍ፤ ለበርካታ ችግሮች አለመቀረፍ እንደ ሰበብ የሚቀርበውን የገንዘብ እጥረት ማህበረሰቡን ቀጥተኛ ተሳታፊ በማድረግ መፍትሄ መስጠት የመቻልን ክህሎት በተግባር እንዲያጎለብቱ ያደርጋል። በመሆኑም ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ አምራችና ችግር ፈች ዜጎች ይሆናሉ።

በዚህ ለሌሎች ተቋማት አርያ በሚሆን ተግባር ተማሪዎች በርካታ ስራዎችን በመስራት ለተጠቃሚዎች በማስረከብ ላይ ይገኛሉ።

date: 
Saturday, March 12, 2022 - 11:30

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University