እንኳን ደስ አላችሁ!! እንኳን ደስ አለን!!!

(የካቲት 19፣2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር)፦ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሲያስተምራቸው የነበሩትን ተማሪዎች አስመርቋል።

የእለቱ የክብር እንግዳ ዶ/ር አየለ ተሾመ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴዔታ ለተመራቂዎች ቁልፍ መልክት አስተላልፈውዋል።

ኮሌጁ 383 በቅድመ-ምረቃ፣ 24 በማስተርስ እንዲሁም በሕክምና ስፔሻሊቲ 50 በድምሩ 457 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን ከተመራቂዎች መካከል 187ቱ ሴቶች ናቸው።

ኮሌጁ ከተቋቋመበት ጀምሮ በቅድመ-ምረቃ 2456፣በድህረ-ምረቃ 805፣ በሕክምና ስፔሻሊቲ 219፣ በሶስተኛ ዲግሪ 6፣በድምሩ 3486 ተማሪዎችን አስመርቋል። ከተመራቂዎች መካከልም 951 የሚሆኑት ሴቶች ናቸው።

የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሀገሪቱን የጤና ስርዓት ለማሻሻል፣ ለማህበረሰቡ ጥራት እና ተደራሽነት ያለው የሕክምና አግልግሎት መስጠት የሚችሉ ባለሙያዎችን በማፍራት የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል።

በአሁኑ ሰዓት ኮሌጁ 2363 ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል።

date: 
Saturday, February 26, 2022 - 01:45

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University