ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 7 ሺህ 520 ተማሪዎቹን አስመረቀ፡፡ Bahir Dar University held graduation for 7,520 of its students

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛ፣ በተከታታይ ትምህርት፣ በክረምትና በርቀት መርሐ-ግብሮች ትምሕርታቸውን ያጠናቀቁ 7 ሺህ 520 ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት በበይነ-መረብ በተካሔደ ደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል፡፡ 4 ሺህ 543 በቅድመ-ምረቃ፣ 2 ሺህ 254 በድሕረ-ምረቃ 2ኛ ዲግሪ፣ 41 በስፔሻሊቲ፣ 40 በሦስተኛ ዲግሪ (ፒ.ኤች.ዲ)፣ 522 በሰርተፊኬት (ፒ.ጂ.ዲ.ቲ) እና 120 በኤች፣ዲ፣ፒ የተመረቁ ሲሆን ከአጠቃላይ ተመራቂዎች መካከልም 466 ያህሉ በዩኒቨርሲቲው ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሕክምና ት/ት ቤት፣ በጤና ሳይንስ ት/ት ቤት እና በሕብረተሰብ ጤና ት/ት ቤት ትምሕርታቸውን የተከታተሉ ናቸው፡፡

የምረቃ መርሐ-ግብሩን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩ ሲሆን በማስከተልም የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢ.ፌ.ዴሪ. ውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ኢንጂኔር ስለሺ በቀለ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በዕለቱ በሕክምና ከተመረቁ 466 ተማሪዎች መካከል በትምሕርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅና ተሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት ዶ/ር ዘላለም አዲስ አጠቃላይ ውጤት 3.73፣ ዶ/ር ማስረሻው ቦጋለ አጠቃላይ ውጤት 3.62 እንዲሁም ዶ/ር አዲስዓለም ሀብታም አጠቃላይ ውጤት 3.60 በማግኘት ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ ዶ/ር ቤተልሔም ይትባረክ ከሴት ተማሪዎች የላቀ ውጤት (3.57) በማምጣት የምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ዘንድሮ ለሶስተኛ ጊዜ ባዘጋጀው ተጨማሪ የእውቅና መርሐ-ግብር በኢንተርንሽፕ ቆይታቸው የላቀ የሕክምና አገልግሎት ስራ አፈፃፀም ላስመዘገቡ 10 ሐኪሞች (ዶ/ር አስከብር መኬ፣ ዶ/ር ተመስገን ሹሜ፣ ዶ/ር አየንሽ ይሁኔ፣ ዶ/ር አዲስዓለም ሀብታም፣ ዶ/ር በቃሉ ዓለሙ፣ ዶ/ር ናሆም መስፍን፣ ዶ/ር አብደላ ሞሐመድ፣ ዶ/ር ሰላማዊት ጀምበር፣ ዶ/ር ወርቅነሕ አምሳሉ እና ዶ/ር አበባው እሸት) እውቅና ሰጥቷል፡፡

አሜሪካን አገር በሚገኘው የሐኪም ወርቅነሕ-መላኩ በያን ሶሳይቲ አዘጋጅነት በእውቁ የሕክምና ባለሙያ ፕሮፌሰር እደማርያም ፀጋ ተሰይሞ የላቀ ውጤት ላስመዘገበ/ች የሕክምና ተማሪ በየዓመቱ መበርከት የጀመረው የፕሮፌሰር እደማርያም ፀጋ አካዳሚክ ኤክሰለንስ ሽልማት አጠቃላይ ውጤት 3.73 ላስመዘገበውና በዕለቱ ደምቆ ለዋለው ዶ/ር ዘላለም አዲስ ተሰጥቷል፡፡ ይህም የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ሽልማትን ያካተተ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ዘላለም አዲስ በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የላቀ ውጤት አምጥተው የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ መሆን ከቻሉት ሁለት ተመራቂዎች አንዱ በመሆን በክብር እንግዳው የወርቅ ሜዳሊያ ተበርክቶለታል፡፡  

የባሕር ዳር የኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዛሬው ዕለት ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለተመረቃችሁ ተማሪዎችና ለቤተሰቦቻችሁ በሙሉ እንኳን ደስ ያላችሁ ይላል፡፡
*************************************************************************************

Bahir Dar University held its virtual graduation ceremony for 7,520 students who completed their studies in regular, continuing education, summer, and distance education programs. This is an aggregate of 4,543 undergraduate, 2,254 post-graduate Master’s degree, 41 specialty, 40 PhD, 522 certificate (PGDT) and 120 HDP graduates. Of all, 466 graduates attended in Medicine, Health Sciences, and Public Health schools of College of Medicine and Health Sciences.

The graduation event started with an opening remark by Dr. Firew Tegegne, President of Bahir Dar University. Following, guest of honor Dr. Eng. Sileshi Bekele, Minister of F.D.R.E Ministry of Water, Irrigation, and Energy, and President of Bahir Dar University Board delivered messages to graduates and their families.  

On the event, best achieving graduates of College of Medicine and Health Sciences were acknowledged. Dr. Zelalem Addis (CGPA 3.73), Dr, Masreshaw Bogale (CGPA 3.62) and Dr. Addisalem Habtam (CGPA 3.60), ranked 1 to 3 respectively, were handed Best Performance Award while Dr. Betelhem Yitbarek (CGPA 3.57) was awarded for her outstanding achievements among all female graduates of Doctor of Medicine.

Ten graduates of the College (Dr. Askebir Mekie, Dr. Temesgen Shumie, Dr. Ayenesh Yihunie, Dr. Addisalem Habtam, Dr. Bekalu Alemu, Dr. Nahom Mesfin, Dr. Abdela Mohamed, Dr. Selamawit Jember, Dr. Workneh Amsalu, and Dr. Abebaw Eshet) received Best Intern of the Year certificates in recognition of their best internship performances.

Dr. Zelalem Addis (CGPA 3.73) won the Professor Edemariam Tsega Academic Excellence Award, which is sponsored by the American-based Hakim Workneh- Melaku Beyan Society. The prize, named after the famous physician Professor Edemariam Tsega, has been awarded for the first time. Dr. Zelalem also received a gold medal from the hands of the guest of honor for his exceptional achievements throughout his stay at Bahir Dar University.

College of Medicine and Health Sciences, Bahir Dar University congratulates all graduates of Bahir Dar University and their families.

Date: 
Saturday, August 29, 2020 - 13:00
images: 

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University