Extension

በማታ መርሀ-ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት መግቢያ መስፈርት

  •  12 ክፍል ዉጤት የሚመዘገቡ ተማሪዎች ፈተና በወሰዱበት አመት የት/ት ሚኒስቴርን የከፍተኛ ትምህርት የመግቢያ መስፈርት ያሟሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  • ድግሪ አስይዘዉ ለሚመዘገቡ አመልካቾች በማንኛዉም የትምህርት መስክ መመዝገብ ይችላሉ፡፡
  • ዲፕሎማ አስይዘዉ ለሚመዘገቡ አመልካቾች በዲግሪ መርሃ-ግብር መመዝገብ የሚችሉት ዲፕሎማቸዉ ቀጥተኛ ተዛምዶ ሲኖረዉ ነዉ፡፡
  • በ 12ኛ ክፍል ዉጤት ከሚመዘገቡ ተማሪዎች በስተቀር ሁሉም አመልካቾች ቢያንስ የ1 ዓመት የስራ ልምድ ማስረጃ ህጋዊ እዉቅና ካለዉ መስሪያ ቤት(ድርጅት) ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
  • ዲፕሎማ አስይዘዉ ለሚመዘገቡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲዉን የመግቢያ ፈተና ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን የዲግሪ እና 12ኛ ክፍል የትምህርት ዝግጅት ያላቸዉ የመግቢያ ፈተና እንዲወስዱ አይጠበቅባቸዉም፡፡
  • ዲግሪ ወይም ዲፕሎማ አስይዘዉ ለሚመዘገቡ አመልካቾች፣ በማመልከቻ ወቅት Official Transcript መድረስ ይኖርበታል፡፡
  • የማመልከቻ ክፍያ (Admission Fee) አይመለስም፡፡
  • በአስረጅነት የሚቀርቡ ማንኛዉም መረጃዎች ኦርጅናሉንና ከሁለት ፎቶ ኮፒ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርባቸዋል፡

የመሰናዶ ፈተና ለወሰዱ የት/ት ሚኒስቴር የመግቢያ መስፈርት፡-

• በ2010 ዓ.ም 295 እና ከዚያ በላይ
• በ2009 ዓ.ም 295 እና ከዚያ በላይ
• በ2008 ዓ.ም 295 እና ከዚያ በላይ
• በ2007 ዓ.ም 275 እና ከዚያ በላይ
• በ2006 ዓ.ም 250 እና ከዚያ በላይ
• በ2005 ዓ.ም 265 እና ከዚያ በላይ
• በ2004 ዓ.ም 265 እና ከዚያ በላይ
• በ2003 ዓ.ም 265 እና ከዚያ በላይ
• በ2002 ዓ.ም 280 እና ከዚያ በላይ
• በ2001 ዓ.ም 200 እና ከዚያ በላይ
• ከ1995-2000 ዓ.ም የመሰናዶ ፈተና ወስደው ውጤት ያስመዘገቡ

  • ከ1994 ዓ.ም በፊት ዲፕሎማ ያጠናቀቁ
  • ከ1994 ዓ.ም በፊት ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች በዲፕሎማ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ እና ከ1994 ዓ.ም በኋላ ከየትኛውም ተቋም ትምህርታቸውን በ10+3 ወይም በደረጃ -4 ያጠናቀቁ ደረጃ-4 የሙያ ብቃት ማረጋገጫ የሚያቀርቡ