#Exciting_News!!

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው "ዝማምነሽ ታወር" ሕንጻ ከወይዘሮ አፀደወይን በቀለ በሥጦታ ተበረከተለት።

አዲስ አበባ ፡ ታኅሣሥ 09/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ዩኒቨርስቲው የ60ኛ ዓመት ክብረ በዓሉን ሲያከብር ሕዝቡ ተቋሙን ለመደገፍ ትብበር ሊያደርግ እንደሚገባ ያስተላለፈውን መልዕክት ምክንያት በማድረግ የተለያዩ ማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፋቸውን እያበረከቱለት ነው። ከደጋፊዎቹ መካከል ደግሞ ወይዘሮ አፀደወይን በቀለ እና ቤተሰቦቻቸውቀዳሚዎቹ ናቸው።

በባሕር ዳር ከተማ ተወልደው ያደጉት ወይዘሮ አፀደወይን በቀለ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኘውን እና ከእናታቸው ወይዘሮ ዝማምነሽ ወልደየሱስ በውርስ ያገኙትን ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመተውን ዙማምነሽ ታወር ለባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ በስጦታ አበርክተዋል ፡፡

ስጦታውን ለመስጠት ያነሳሳቸውም ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ በጤናው ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎት ለመደገፍ መኾኑን የወይዘሮ አፀደወይን ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡

ስጦታውን የተረከቡት የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፍሬው ተገኝ (ዶ.ር) ዩኒቨርስቲው ትልቅ ኀላፊነት እንዳለበት በመገንዘብ ነው ብለዋል።

ማኅበረሰቡ ያለውን ሃብት ለሕዝብ አገልግሎት ለሚሰጡ ተቋማት በማካፈል ተቋማት ሠፊ አገልግሎት እንዲሰጡ መደገፍ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

ከወይዘሮ አፀደወይን ቤተሰብ ትምህርት በመውሰድ ሁሉም ትብብሩን አጠንክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ ጠቅሰዋል።

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የተሰጠውን የሕንጻ ስጦታ ለማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጥ በማሰብ የእናቶች እና ሕጻናት የሕክምና ማዕከል እንደሚኾን ገልጸዋልዋል።

https://youtu.be/mIUCRHnKM-s?si=s6gCuKA31ZL8wj1Y

date: 
Tuesday, January 9, 2024 - 06:30

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University