ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ
==============================
07/08/2016ዓ.ም 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካች መምህራንን አወዳድሮ የፋርማሲ አገልግሎት እና ትምህርት ዲሬክተር (Director, Clinical Pharmacy Services and Education) ቦታ መመደብ ይፈልጋል፡፡

የማወዳደሪያ መሥፈርት
==============

1ኛ. የትምህርት ደረጃ ሁለተኛ ዲግሪ/ሶሥተኛ ዲግሪ (ወይም አቻ) እና ከዚያ በላይ ማዕረግ ያለው/ያላት መምህር፣ 
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በጤና ተቋማት፣ በመማር ማስተማር፣ ሕክምናና ማኅበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣ 
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ (የፋርማሲ አገልግሎት እና ትምህርት) ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የፋርማሲ አገልግሎትና ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትሐዊነት፣ ጥራትንና ደኅንነት፣ ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ኮሌጁን የሕክምና አገልግሎት እና የትምህርት የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እና ክሱትነቱን ለመጨመር፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ (ስልታዊ) ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣ 
4ኛ. ከኮሌጁ የሚሰጠውን ዝርዝር ኃላፊነት በቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት ተቀብሎ በከፍተኛ ብቃት የሚፈፅም፣
5ኛ. የኮሌጁ አመራሮች፣ የሆስፒታል ማኔጅመንት አባላት፣ የፋርማሲ ትምህርት እና አገልግሎት ሠራተኞች ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፣
6ኛ. ከትምህርት ወይም ምርምር ወይም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መደበኛ የሥራ እረፍት ላይ ያልሆነ/ች እና ለቀጣይ ሦስት ዓመት በኃላፊነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች::

አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (07/08/2016ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት ዐሥራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት የሚከተሉትን ሰነዶች ማለትም
1. ማመልከቻ ደብዳቤ፣
2. ግለ ታሪክ ('CV')፣
3. የትምህርትና የሥራ/አመራርነት ልምድ (በሰው ሀብት አስተዳድር ልማት ቢሮ የረጋገጠ) ማስረጃ ፎቶ ኮፒ  እንዲሁም
4. ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ
በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ድሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የመመዝገቢያ ቦታ
==========
ጥበበ ግዮን ካምፓስ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
ባሕር ዳር

#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!

Follow us on:

Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu?mibextid=ZbWKwL
Website:
bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information_office_CMHS_BDU
Twitter:
twitter.com/medicine_bdu?t…
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/college-of-medicine-and-health-sciences...

date: 
Sunday, April 14, 2024 - 23:00

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University