ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ 
==============================
07/08/2016ዓ.ም 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት ማሳለጥ ድሬክተር ቦታ መመደብ ይፈልጋል፡፡ 

የማወዳደሪያ መሥፈርት 
==============

1ኛ. የትምህርት ደረጃ ሁለተኛ ዲግሪ/ሶሥተኛ ዲግሪ/ስፔሻሊቲ ሰርተፊኬት (ወይም አቻ) እና ከዚያ በላይ ማዕረግ ያለው/ያላት፣  
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በጤና ተቋማት፣ በመማር ማስተማር፣ ሕክምናና ማኅበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣  

3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ (የሕክምና አገልግሎት ማሳለጥ ዲሬክቶሬት እና በሥሩ የያዛቸውን ዴስኮች ማለትም ማዕከላዊ የሕክምና መሳሪያዎች እና ግብአቶች÷ የአልባሳት አቅርቦት አጠቃቀምና ጥራት ክትትል÷ የሥነ ምግብ ሕክምና ጥራት ክትትል እና የታካሚዎች ምግብ ዝግጅት እና አገልግሎት) ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የሕክምና አገልግሎት ተደራሽነት፣ ፍትሐዊነት፣ ጥራትንና ደኅንነት፣ ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ሆስፒታሉን የሕክምና አገልግሎት የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እና ክሱትነቱን ለመጨመር፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ (ስልታዊ) ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣  

4ኛ. ከኮሌጁ የሚሰጠውን ዝርዝር ኃላፊነት በቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት ተቀብሎ  በከፍተኛ ብቃት የሚፈፅም፣ 
5ኛ. የኮሌጁ አመራሮች፣ የሆስፒታል ማኔጅመንት አባላት፣ የኮሌጁና የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፣ 
6ኛ. ከትምህርት ወይም ምርምር ወይም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መደበኛ የሥራ እረፍት ላይ ያልሆነ/ች እና ለቀጣይ ሦስት ዓመት በኃላፊነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች::

አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (07/08/2016ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት ዐሥራ አምስት (15) ተከታታይ ቀናት የሚከተሉትን ሰነዶች ማለትም 

1. ማመልከቻ ደብዳቤ፣
2. ግለ ታሪክ ('CV')፣ 
3. የትምህርትና የሥራ/አመራርነት ልምድ (በሰው ሀብት አስተዳድር ልማት ቢሮ የረጋገጠ) ማስረጃ ፎቶ ኮፒ  እንዲሁም
4. ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ
በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ድሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

የመመዝገቢያ ቦታ 
==========
ጥበበ ግዮን ካምፓስ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 
ባሕር ዳር

#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!

Follow us on: 

Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu?mibextid=ZbWKwL
Website: 
bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information_office_CMHS_BDU
Twitter:
twitter.com/medicine_bdu?t…
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/college-of-medicine-and-health-sciences...

date: 
Friday, April 12, 2024 - 06:00

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University