ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ 
===================
18/06/2016 ዓ.ም 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ የኮሌጁ የጤና ትምህርት ኮርፓሬት ም/ድሬክተር (Deputy Corporate Director, Medical and Health Science Education) ቦታ መመደብ ይፈልጋል፡፡ 

የማወዳደሪያ መሥፈርት 
==============

1ኛ. የትምህርት ደረጃ ሦስተኛ ዲግሪ/ስፔሻሊቲ ሰርተፊኬት (ወይም አቻ ) እና ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ በላይ ማዕረግ ያለው/ያላት፣  
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በጥናትና ምርምር ወይም መሰል ተቋማት፣ በመማር ማስተማር፣ ሕክምናና ማኅበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣  
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የጤና ትምህርት  ተደራሽነት፣ ፍትሐዊነት፣ ጥራትንና ደኅንነት፣ ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ኮሌጁን የጤና ትምህርት የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እና ክሱትነቱን ለመጨመር፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ (ስልታዊ) ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣  
4ኛ. ከኮሌጁ የሚሰጠውን ዝርዝር ኃላፊነት በቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት ተቀብሎ  በከፍተኛ ብቃት የሚፈፅም፣ 
5ኛ. የኮሌጁ አመራሮች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የኮሌጁ መምሕራን ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፣ 
6ኛ. ከትምህርት ወይም ምርምር ወይም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መደበኛ የሥራ እረፍት ላይ ያልሆነ/ች እና ለቀጣይ ሦስት ዓመት በኃላፊነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች::

አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (18/06/2016ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት ዐሥራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከተሉትን ሰነዶች ማለትም 
1. ማመልከቻ ደብዳቤ፣
2. ግለ ታሪክ('CV')፣ 
3. የትምህርትና የሥራ/አመራርነት ልምድ (በሰው ሀብት አስተዳድር ልማት ቢሮ የረጋገጠ) ማስረጃ ፎቶ ኮፒ  እንዲሁም
4. ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ
በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ድሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

የመመዝገቢያ ቦታ 
==========
ጥበበ ግዮን ካምፓስ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲ
ባሕር ዳር

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University