ማስታወቂያ

30/08/2015ዓ.ም

ማስታወቂያ/Vacancy/

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምክትል የሚድዋይፍሪ አገልግሎት ዲሬክተር (Vice Director, Midwifery Services) ቦታ መሾም ይፈልጋል፡፡

የማወዳደሪያ መስፈርት
----------------------

1ኛ. የትምህርት ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ/ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያለው/ያላት፣
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት/ጤና ተቋም፣ በሆስፒታል፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት በመማር ማስተማር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ሀላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች ወይም ዉጤት ያመጣ/ያመጣች፣
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የነርስ አግልግሎትን እና ተደራሽነትን፣ ፍትሃዊነት፣ ጥራትን፣ ተገቢነትንና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ኮሌጁን፣ ሆስፒታሉንና ትምህርት ቤቶችን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣
4ኛ. ከኮሌጁ የሚሰጠውን ዝርዝር  ሃላፊነት በጥበብ፣ በቅንነት፣ በቁርጠኝነት እና በታማኝነት ተቀብሎ የሚፈፅም፣
5ኛ. የሆስፒታሉ አመራሮች፣ የሆስፒታሉ ማኔጅመንት አባላት፣ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፡፡

አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (30/08/2015ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የትምህርትና የሥራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የመመዝገቢያ ቦታ
------------------
ጥበበ ግዮን ካምፓስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር ቢሮ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University